ባለቀለሟ፣ ተወዳጇና ሳምንታዊዋ የማክሰኞ እትም ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ዛሬም ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ ከእጃችሁ ትደርሳለች፤ ለመሆኑ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን? ከሀገር ውስጥ፡- ሀትሪክ ስፖርት ባሳለፍነው እሁድ የመጋበዝ እድል ስላገኘችበትና ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በደመቁበት የኦቷዋ ማራቶን ሰፋ ባለ መልኩ ዘገባን ይዘን የቀረብን ሲሆን በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 24ኛ ሳምንት የሳምንቱ ምርጥ ጨዋታ መካከል ደደቢት ከ ኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ወሳኝ ፍልሚያ የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ስለ ጨዋታው እሚሉት ነገር ለሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የሰጡት ቃለ-ምልልስ ስላለ እሱንም አቅርበንላችኋል፤
ከባህር ማዶ ሪያል ማድሪድ በነገሰበት የኪዬቭ ከተማ ፍፃሜን አስመልክቶ የሚወዱት ዘገባ ተሰርቷል፤ ሌሎች የባህር ማዶ ዘገባዎችንም ሀትሪክ ይዛለች፤ አታምልጦት፡፡
የነዛሬው የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ /ምስል/ ይህንን ይመስላል፡፡

አስተያየት ይስጡ