በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እየተመሩ በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆናቸውን እያሳዩ የቆዩት የጣናው ሞገዶች የሁለት ተጨዋቾቻቸውን ውል ማራዘማቸው ተገልጿል ።
በዘንድሮው የውድድር ዓመት በመሀል ሜዳው በክለቡ ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴን ሲያሳይ የቆየው ፍቅረ ሚካኤል ዓለሙ እና የዜናው ፈረደን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ማራዘማቸውን ለማወቅ ተችሏል ።
ባህርዳር ከነማ የአሰልጣኛቸውን ፋሲል ተካልኝ ውል ማራዘማቸው ሲታወስ ሊጉ እሰከ ተቋረጠበት እለት ሊጉን 27 ነጥብ ይዘው በአምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ይገኙ ነበር ።
አስተያየት ይስጡ