ባህር ዳር ከተማ የወሳኝ ተጫዋቾቹን ውል አራዝሟል !

የጣናው ሞገዶቹ በዝውውሩ የበርካታ ተጫዋቾቻቸውን ውል ሲያራዝሙ በዛሬው ዕለት የሶስት ተጫዋቾቻቸውን ውል ማራዘማቸው ተሰምቷል ።

በዘንድሮው የውድድር ዓመት ባጋጠመው ጉዳት ጨዋታዎች ቢያልፉትም ከመስመር እየተነሳ ጥሩ እንቅስቃሴን ሲያደርግ የቆየው ሳለአምላክ ተገኝ በጣና ሞገዶቹ ቤት ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት ተስማምቷል ።

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ከተለያየ በኋላ ባህርዳር ከተማን በመቀላቀል በመሐል ሜዳ ክፍሉ ላይ ብቃቱን ያሳየው ሳምሶን ጥላሁን እንዲሁም ሳሙኤል ወዴሳ በዛሬው ዕለት ውሉን ያራዘሙ ሌሎች ተጫዋች ነው ።

የጣና ሞገዶቹ እስከ አሁን ባለው የዝውውር ሂደት የስምንት ተጫዋቾችን ውል ለማራዘም ችለዋል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor