ባህር ዳር ከተማ የአጥቂውን ውል አድሷል !!

 

የዝውውር መስኮቱ ዘግይተው ቢቀላቀሉም ንቁ ተሳትፎን በማድረግ ላይ የሚገኙት የጣና ሞጎዶቹ የአጥቂያቸውን ውል ማደሳቸው ተሰምቷል ::

በዝውውር መስኮቱ የአምስት ነባር ተጫዋቾችን ውል ያደሱት የጣና ሞገዶቹ ከደቂቃዎች በፊት የአጥቂያቸውን ወሰኑ ዓሊ ውል ማደሳቸው ተገልጿል።

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት ባህር ዳር ከተማዎች እስካሁን የፍቅረሚካኤል ዓለሙ ፣ የዜናው ፈረደ ፣ አቤል ውዱ ፣ የደረጄ መንግስቱ እና የኃይለየሱስ ይታየውን ውል ለተጨማሪ 2 ዓመት ለማደስ መስማማታቸው ይታወሳል።

ከደቂቃዎች በፊት የፊት መስመር አጥቂውን ወሰኑ ዓሊን ውል ለቀጣዩ ሁለት ዓመት ማደሳቸው ተሰምቷል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor