ባህርዳር ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ላለው የአስረኛ ሳምት ጨዋታ ወደ አዲስ አበባ የማቅናቱ ጉዳይ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።
ባሳለፍነው ሳምንት በደሞዝ ክፍያ ምክንያት ልምምዳቸውን አቁመው የነበሩት የባህርዳር ተጫዋቾች የሶስት ወር ደሞዛችን ካልተከፈለን አንጫወትም ብለው የነበረ ሲሆን የአንድ ወር ደሞዛቸው ተከፍሎ ቀሪው የሁለት ወር ደግሞ ወልዋሎን ገጥመው 3-2 ካሸነፉበት ጨዋታ በኃላ እንደሚከፈላቸው ቃል ቢገባላቸውም እስካሁን ደሞዛቸው እንዳልተከፈላቸው ነው የሰማነው። በዚህም መሰረት ተጫዋቾቹ ጠዋት ላይ ልምምድ ቢሰሩም ደሞዛቸው ካልተከፈላቸው ከዛሬ ጀሞሮ ልምምድ እንደማይሰሩ እና ወደ አዲስ አበባ በማቅናት ቅዱስ ጊዮርጊስን እንደማይገጥሙ ተጫዋቾቹ ለክለቡ አመራሮች አሳውቀዋል።
አስተያየት ይስጡ