ባህርዳር ከተማ በግብ ጠባቂው ሀሪስተን ሄሱ ጉዳይ ላይ ለፌደሬሽኑ የቅሬታ ደብዳቤ አስገብቷል

 

ባህርዳር ከተማ በግብ ጠባቂው ሀሪስተን ሄሱ ፌደሬሽኑ ያለውን ውሳኔ ያሳውቀኝ በማለት ለፌደሬሽኑ የቅሬታ ደብዳቤ አሰገብቷል።

በ 10ኛ ሳምንት ጨዋት ወደ አዲስ አበባ አቅንቶ ቅዱስ ጊዮርጊስን የገጠመው ባህርዳር ከተማ ግብ ጠባቂው ሀሪስተን ሄሱ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ቢካተትም አሟምቀው ወደ መልበሻ ክፍል ካመሩ በኋላ ወደ ጨዋታ ለመግባት ዝግድት በሚያደርጉበት ወቅት የእለቱ ዳኛ ቴዎድርስ ምትኩ ጋር በውስጥ የለበሰውን መለያ እንዪያወጣ ቢነግሩትም እሰጣ ገባ ውስጥ በመግባቱ ምክንያት ከጨዋታ ጅማሮ በፊት የቀይ ካርድ ሰላባ መሆን። በምትኩ ግብ ጠባቂው ፅዮን መርዕድ ግቡን እንዲጠብቅ መደረጉ ይታወሳል። ሆኖም ግን አወዳዳሪው አካል የተጫዋቹ ቅጣት ተመለከተ ለፌደሬሽኑ ደብዳቤ ብንልክም መልስ ለክለባችን ባላማሳወቁ ምክንያት ለተጫዋቾች ምርጫ ተቸግሯል ሲል ነው ይህ የቅሬታ ደብዳቤ የላከው። ተጫዋቹ ሶስት ጨዋታዎች ላይ ያልተሳተፈ ሲሆን በነገው እለት ከሰበታ ከተማ ጋር ባለን ጨዋታ ውሳኔው እስካልደረሰን ድረስ መጠቀም አለብን ብሏልተ

ክለቡ የላከው ደብዳቤ የሚከተለው ይመስላል👇👇👇👇👇

 

 

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor