ባህርዳር ከተማ ሄኖክ አወቀን አስፈርሟል

ባህርዳር ከተማዎች በወልቂጤ ከተማ በቂ የመሰለፍ እድል ያላገኘውን ሄኖክ አወቀን አስፈርመዋል።ቀድሞው የፋሲል ከተማ፣ኢኮስኮ የመስመር አማካኝ ሄኖክ አወቀ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በመጀመሪያዎቹ ጨዋታዎች ላይ የክትፎዎቹ ወሳኝ ተጨዋች መሆን ችሎ የነበረ ቢሆንም ከመጀመርያው ዙር ግማሽ ጨዋታዎች በኃላ በቂ የመሰለፍ ዕድል አለማግኘቱን ተከትሎ ከክለቡ ጋር ሊለያይ ችሏል።

 

የጣና ማገዶቹ ሊጠናቀቅ 16 ቀናት በቀሩት የግማሽ ውድድር ዓመት የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ላይ የመጀመርያ ፈራሚያቸውን ሄኖክ አወቀ ማድረግ ሲችሉ በቀጣይ ቀናቶሽም ተጨማሪ ዝውውሮችን ሊያከናውኑ እንደሚችሉ ይገመታል።

Hatricksport website writer

Twitter

ዳዊት ብርሀነ

Hatricksport website writer