ቡናማዎቹ ኮከባቸውን ለማቆየት ተስማሙ !
ያለፉትን ዓመታት ኢትዮጵያ ቡናን በአምበልነት በመምራት ለቡድኑ ስኬት ትልቅ ሚናን ሲጫወት የቆየው አማኑኤል ዮሐንስ በኢትዮጵያ ቡና ለተጨማሪ አራት ዓመታት ለመቆየት መስማማቱ ይፋ ሆኗል ።
አማኑኤል ዮሐንስ ከወራት በፊት ለፋሲል ከነማ ለመጫወት ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ዝውውሩ ከመስከረም 2 በፊት የማይፀድቅ በመሆኑ በይፋ ውሉን በቡናማዎቹ ቤት አራዝሟል ።