Oumed Oukri of Ethiopia during the 2013 African Cup of Nations Group C match between Ethiopia and Nigeria at the Rustenburg Stadium in Rustenburg, South Africa. Photo: VISIONHAUS/Ben Radford
መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ “በግብፅ ምርጥ የእግር ኳስ ጊዜን እያሳለፍኩ ነው” ዑመድ ኡክሪ የግብፁ (EL-ENTAG EL HARBY)
ዋልያዎቹ

“በግብፅ ምርጥ የእግር ኳስ ጊዜን እያሳለፍኩ ነው” ዑመድ ኡክሪ የግብፁ (EL-ENTAG EL HARBY)

አጋራ
አጋራ

የግብፅ ፕሪምየር ሊግ ላይ ለኢል ኢንታግ
ኢል አርቢ ክለብ በመጫወት ላይ የሚገኘው
ዑመድ ኡኩሪ

Oumed Oukri of Ethiopia during the 2013 African Cup of Nations Group C match between Ethiopia and Nigeria at the Rustenburg Stadium in Rustenburg, South Africa. Photo: VISIONHAUS/Ben Radford

 

የአንደኛው ዙር ውድድር
መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ ለእረፍት
ወደ ሀገሩ የመጣ ሲሆን ተጨዋቹ የቀጣይ
ጊዜ የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ሕይወቱን
ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ለማድረስና ወደሌሎች
ሀገራትም ተጉዞ ለመጫወት እንዲችል
ጠንክሮ እንደሚሰራም ይናገራል፤ የግብፅ
ሊግ ላይ በአሁን ሰዓት በጥሩ ብቃቱ ላይ
የሚገኘው ኡመድ ኡኩሪ በሀገሪቱ ቆይታው
ለአልኢትአድ አሌክሳንደሪያና ለኢኤንፒፒአይ
ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን ተጨዋቹን
ለእረፍት በመጣበት የአሁን ሰአት ላይ
ስለክለቡ ቆይታውና ስለ ወቅታዊ አቋሙ
ጠይቅነው የሚከተለውን ምላሹን ሰጥቶናል፡፡
ሀትሪክ፡- እንኳን ደህና መጣህ?
ዑመድ፡- እንኳን ደህና ቆያችሁኝ፡፡
ሀትሪክ፡- የግብፅ ሊግ አጠቃላይ ቆይታህ
ምን ይመስላል?
ዑመድ፡- የግብፅ የእስካሁን ቆይታዬ በጣም
አሪፍና ጥሩም ነው፤ በሀገሪቱ የሊግ ውድድርም
በችሎታዬ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ መሻሻሎችንም
አይቼበታለሁ፡፡ ወደፊት ደግሞ ከእዚህ በላይም
በመጓዝ ከፍተኛ ደረጃ ላይም እደርሳለው ብዬም
ነው የማስበው፡፡
ሀትሪክ፡- የግብፅ ሊግ ላይ ክለባችሁ ኢል
ኢንታግ ኢል አርቢ እያደረገ ስላለው ተሳትፎስ
ምን ትላለህ?
ዑመድ፡- የግብፅ ሊግ ውስጥ ቡድናችን
በአሁን ሰዓት ምንም እንኳን በደረጃው ሰንጠረዥ
ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ባይገኝም ጠንካራ ከሚባሉት
ክለቦች መካከል ግን ስሙ የሚጠቀስ ነው፤ የሊጉ
ውድድር ሲጀመር በአራትና አምስት ጨዋታዎች
ያህል ተደጋጋሚ ነጥቦችን ጥለን ነበር፤ ከእዚያ
በኋላ ግን ተጠናክረን በመቅረብ የአሁን ሰዓት
ላይ በጥሩ ብቃት ላይ ነው የምንገኘው፡፡
ሀትሪክ፡- የክለባችሁ ተሳትፎ ውስጥ አንተስ
እየሰጠህ ያለው ግልጋሎት ምን ይመስላል?
ዑመድ፡- የግብፅ ሊግ ውስጥ ለክለቤ
እየሰጠሁት ያለው ግልጋሎት በጥሩነቱ የሚጠቀስ
ነው፤ ክለባችን ብዙውን ጊዜም የሚያጠቃው
በእኔ በኩል ነው፤ ለእዚያም ስል ሁሌ ራሴን
በጥሩ መልኩም አዘጋጀዋለው፤ ውድድሩ
ሲጀመር ለሁለትና ለሶስት ጨዋታዎች ያህል
የተጠባባቂ ወንበር ላይ በመሆን ነበር ተቀይሬ
በመግባት የምጫወተው፤ በኋላ ደግሞ የጌች
ቡድንን ገጥመን ድል ባደረግንበት ጨዋታ ላይ
ምርጥ ብቃቴን በማሳየቴና ያም ብቃቴ ሌሎች
ግቦችንም እያስቆጠርኩ እንድመጣ ስላስደረገኝም
የአሁን ሰዓት ብቃቴን በጣም እየወደድኩትም
ነው የሚገኘው፡፡
ሀትሪክ፡- እስከአሁን ለክለብህ ስንት ግቦችን
አስቆጥረሃል?
ዑመድ፡- የግብፅ ሊግ የእስካሁን ተሳትፎዬ
ላይ ለክለቤ አራት ያህል ግቦችን አስቆጥሬያለሁ፡
፡ ከእዚያም ውጪ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችንም
ለቡድኔ ተጨዋቾች ማቀበልም ችያለውና
በሁለቱም በኩል እየተሳካልኝም ነው፡፡
ሀትሪክ፡- በግብፅ ሊግ የእግር ኳስን በባዶ
ስታድየም ያለ ተመልካች ነው እየተጫወታችሁ
የምትገኙትና ያለው ስሜት ምን ይመስላል?
ዑመድ፡- የግብፅ ሊግ ላይ የእግር ኳስን
ስንጫወት ተመልካቾችና የቡድናችን
ደጋፊዎች ወደሜዳ አይግቡ እንጂ ግጥሚያዎቹ
በተለያዩ ቻናሎች ለምሳሌ በናይል ስፖርትና
በሌሎችም በቀጥታ ስለሚተላለፍ ህዝቡ
ኳሱን በደንብ ይከታተላል፤ እነሱ ከውጪ
ኳስ ይልቅ የአገራቸውን ሊግም ነው
በሚገባም የሚከታተሉትና ጥሩ ብቃትህን
ስታሳይ ይወዱሃል፤ ጥሩ ስትጫወትና ጎል
ስታስቆጥርም በደንብም ያበረታቱሃል፡፡
ሀትሪክ፡- በአሁን ሰዓት በግብፅ ሊግ
ቆይታህ በጣም ደስተኛ ነህ?
ዑመድ፡- አዎን፤ በተለይ ደግሞ
የአሁኑ ሰአት ላይ ጥሩ ብቃቴን እያሳየሁ
ስለሆነም በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡
ሀትሪክ፡- በግብፅ ብቸኛ ኢትዮጵያዊያን
ተጨዋቾች አንተና ሽመልስ ከመሆናችሁ
አንፃር የብቸኝነቱ ስሜት አይሰማህም?
ዑመድ፡- የብቸኝነቱ ስሜት የዛሬ
ሶስት ዓመታት ላይ እንጂ አሁን ፈፅሞ
አይሰማኝም፤ ያኔም እኔና ሽመልስ
የምንኖርበት ቦታ የተራራቀ ስለነበርና
የማወራው ሰውም ስለሌለም ነበር ብቸኝነቱ
ይሰማኝ የነበረው፤ አሁን ግን መኖሪያችን
አጠገብ ለአጠገብ ስላለና በተደጋጋሚም
የምንገናኝበት ጊዜም ስላለ የአሁን ሰዓት ላይ
ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ነው የሚገኘው፤
ምንም የምጎዳበት ነገርም የለም፡፡
ሀትሪክ፡- የሽመልስ በቀለን ብቃት
እንዴት አገኘኸው?
ዑመድ፡- ሽሜ በአሁኑ ወቅት በጥሩ
ብቃት ላይ ነው የሚገኘው፤ የቡድኑ ቁልፍና
ወሳኝም ተጨዋች ሆኗል፤ ጎሎችንም
ለክለባቸው እያስቆጠረላቸው ስለሆነ ከፍተኛ
ዝናንም በሀገሪቱ ሊግ ውስጥ እያተረፈም
ይገኛል፡፡
ሀትሪክ፡- በግብፅ ሊግ ወደፊት ከአንተ
ምን እንጠብቅ? ስለቀጣይ የፕሮፌሽናል
ተጨዋችነት ሕይወትህስ ምን ታስባለህ….
ዑመድ፡- የግብፅ ሊግ ላይ አሁን
እያሳየሁት ያለው ብቃት ጥሩ የሚባል ነው፤
ወደፊት ደግሞ ይህንን ጥሩነቴን አስቀጥዬም
ለመጓዝ ጠንክሬም እሰራለው፤ ጠንክሬም
ስሰራ አሁን ካለሁበት ደረጃ የተሻለ ነገርንም
አገኛለሁ ብዬም አስባለሁ፡፡ የፕሮፌሽናል
ተጨዋችነት ህይወቴን በተመለከተ አሁን
ላይ ሆኜ ሳስብ ያለኝ ብቃት ወደሌሎች
ሀገራት ሄጄ የምጫወትበት እድሉ ይኖረኛል
ብዬም ነው የማስበው፡፡
ሀትሪክ፡- የሀገርህን ብሔራዊ ቡድን
በድጋሚ ለማገልገል ያለህ ፍላጎት የት ድረስ
ነው?
ዑመድ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ
ቡድን ውስጥ ከእዚህ በፊት ተመርጬ
ተጫውቼያለው፤ የሀገሬን ማሊያ ለብሼ
ጥሩ ግልጋሎት መስጠት ደግሞ የሁልጊዜም
ፍላጎቴና ምኞቴ ነው፤ በድጋሚ ተመርጦ
ለመጫወትም ሁሌም ዝግጁ ነኝ፤ ለሀገሬ
መጫወት ደግሞ ግዴታዬም ነውና ይህንን
ወደፊት ዳግም አሳካዋለሁ ብዬ ነው
የማስበው፡፡
ሀትሪክ፡- የግብፅ ሊግ ላይ ቡድናችሁ
ዘንድሮ ምን ውጤት ያመጣል
ዑመድ፡- የግብፅ ሊግ ላይ አሁን ያለን
አቋም ጥሩ ነው፤ የሁለተኛው ዙር ላይም
ጥሩ ብቃታችንን ይበልጥ በማሳየት የሊጉ
ጠንካራ ተፎካካሪ እንደምንሆን እርግጠኛ ነኝ፡

ሀትሪክ፡- የሀገሪቱን የሊግ ፉክክር
እንዴት ነው የምትገልፀው?
ዑመድ፡- የግብፅ ፕሪምየር ሊግ ዘንድሮ
ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ጠንካራ ፉክክርን
እያስተናገደ ነው፤ እዚያ በመሪነት ደረጃም
በወራጅ ደረጃም ላይ የሚገኙት ክለቦች
አንዳቸው በአንዳቸው ላለመሸናነፍ ከፍተኛ
ፍልሚያ ነው የሚያደርጉት ውድድሩም
ጉልበትም የሚጠይቅ ነው፤ ፊትነሱ ከሌለ
ኳሱን መጫወት አትችልምና በእዚሁ መልኩ
ነው እየጠጫወትን የሚገኘው፤ በተለይ
ደግሞ በቅርቡ የግብፅ ብሔራዊ ቡድን
ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈ ስለሆነ የአንደኛውን
ዙር በፍጥነት ለማጠናቀቅ ሲባል በሶስት
ቀን ልዩነት የተጫወትንበት ወቅትም ነበርና
የሊጉ ፉክክር አድካሚም ሆኖ ነው የታየው፡፡
ሀትሪክ፡- በመጨረሻ…
ዑመድ፡- የእግር ኳስን ስጫወት ዛሬ
ለደረስኩበት የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት
ደረጃ እንድበቃ ያስቻሉኝን አካላቶች በሙሉ
አመሰግናለሁ፡፡ ቤተሰቦቼን፣ የፍቅር ጓደኛዬን
እና ፈጣሪዬን እንደዚሁም ደግሞ ከእኔ
ጎን የሚገኘውን ሽመልስ በቀለን ማመስገን እፈልጋለሁ::

images

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...