በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ወቅታዊ መረጃዎች !

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በተለያዩ አጋጣሚዎች እንዲሁም አሁን ላይ የቁርጥ ልጆች እንደሆኑ እያስመሰከሩ የሚገኙት ዑመድ ኡኩሪ እና ሽመልስ በቀለ በግብፅ ሊግ እንዲሁም ቢንያም በላይ በስዊድኑ ኡመያ ክለብ እየተጫወቱ ይገኛሉ ::

የመሐል ሜዳው ፈርጥ ሽመልስ በቀለ ከቀናት በፊት ከኢትዮጵያ ወደ ግብጽ ያመራ ሲሆን ከክለቡ አል መካሳ ጋር ይፋዊ ልምምድ መስራት ጀምሯል ። የግብፅ ሊጎች ከመጀመራቸው አስቀድሞ ክለቦች የወዳጅነት ጨዋታዎችን በማድረግ ላይ ሲገኙ የሽመልስ በቀለ ክለብ አል መካሳ በነገው እለት በቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ዲድዬ ጎሜስ በሚሰለጥነው እስማኤሊያ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል ።

ሌላኛው በግብፅ ሊግ እየተጫወተ የሚገኘው ዑመድ ኡክሪ በአስዋን ክለብ አንጸባራቂ ብቃቱን እያሳየ ቢቆይም ያለፉትን ወራት በከባድ ጉዳት ከሜዳ ተገሎ መቆየቱ ይታወቃል ። ከወደ ግብጽ በወጡ መረጃዎች ዑመድ ኡክሪ ከጉዳቱ በማገገም ቀለል ያሉ ልምምዶችን መስራት መጀመሩን ክለቡ አሳውቋል ። አስዋን ክለብ በዛሬው እለት ከ አረብ ኮንትራክተርስ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ሊያካሂድ ታስቦ የነበረ ቢሆንም ለሌላ ጊዜ መዘዋወሩ ተሰምቷል ።

በአውሮፓዊቷ ስዊድን የመጀመሪያ የውድድር ዓመቱን እያሳለፈ የሚገኘው የመስመር ተጫዋቹ ቢንያም በላይ ከሰዓታት በፊት በተጠናቀቀው የሊጉ መርሀ ግብር ኡመያ ክለብ ሶስት ለ አንድ በሆነ ውጤት ሲያሸንፉ በመጀመሪያው አሰላለፍ በመካተት 89 ደቂቃዎችን በመጫወት አሳልፏል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor