በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ግምገማ የተነሱት ጉዳዮች

 

አሁን በጁፒተር ሆትል ላይ እየተደረገ በሚገኘው የፕሪምየር ሊግ መጀመሪያው ዙር ግምገማ የተለያዩ ሪፖርቶች እየቀሩቡ ሲሆን። ከቀረቡት ሪፖርቶች መሀከል የፕሪምየር ሊጉ የመጀመሪያው ዙር ጠንካራ እና ደካማ ጎን አንዱ ነው። የተነሱትን ነጥቦች በሚከተለው አቅርበናል።

የመጀመሪያው ዙር ጠንካራ ጎን

• ስፖርታዊ ጨዋነት በአንዳንድ ጨዋታዎች ላይ ከተከሰቱት ውጭ በዘንድሮው አመት መልካም የሚባል የስፖርታዊ ጭዋነት ተንፀባርቋል።

• ወጥ የሆነ የጨዋታ ፕሮግራም ሊጉ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች ለማስኬድ ችግር እንደነበረ ቢታወቅም በዝንድሮው አመት ይህ ፍፁም ተሻሽሏል።

• የሚቀርቡ ሪፖርቶች ጥልቅ መሆን ከዚህ ቀደም የተሟላ ሪፖርት ባለመቅረቡ ምክንያት ውሳኔ ለመስጠት የዲስፕሊን ኮሚቴ ከባድ አድርጎበት በሚወስናቸው ውሳኔዎች በርካታ ተቃውሞችን ሲያስተናግድ እንደነበረም ይታወሳል ይህ ግን በዘንድሮው አመት ፍፁም መሻሻሎችን አሳይቷል።

የመጀመሪያው ዙር ደካማ ጎን እና በቀጣዩ ሊስተካከሉ የሚገባቸው ነገሮች

የጥቂት ክለቦች የሜዳ ችግር

• ለኮሚሽነሮች ግልፅ እና ለእይታ ምቹ የሆነ ቦታ መፍጠር

• ከክለቦች አርማ ውጪ ምንም አይነት የፖለቲካ ይዘት ያላቸው ነገሮችን ወደ ስታድየም እንዳይገቡ ማድረግ

• የተሻሉ የጨዋታ አመራሮችን ትኩረት ለሚሹ ጨዋታዎች መመደብ የሚሉ ከተነሱት ነጥቦች ዋነኞቹ ናቸው።

በፕርሚየር ሊጉ ወሳኔ ያላገኙ ክለቦች

በይግባኝ ሰሚ ኮሜት ተይዘው ውሳኔዎች ያልተሰጡባቸው ጉዳዮች።

የፕርሚየር ሊግ ክለቦች – አራት ክለቦች

ሴቶች ፕርሚየር ሊግ እና ከ 20 አመት በታች ፕርሚየር ሊግ – ዜሮ

ከፍተኛ ሊግ – አራት ክለቦች

አንደኛ ሊግ – አንድ ክለብ

በግለሰብ ደረጃ – ሶስት መሆናቸውን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው አቶ ሙሉጌታ ይፋ አድርገዋል ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor