መነሻ ገጽ ሪፖርት ​በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በመጨረሻው 30ኛ ሳምንት በሜዳው አዳማ ከተማን ያስተናገደው ጅማ አባጅፋር 5-0 በማሸነፍ በመጣ ዓመት የፕሪሚየርሊጉ አሸናፊ ሆኗል። 
ሪፖርትየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግጅማ አባጅፋር

​በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በመጨረሻው 30ኛ ሳምንት በሜዳው አዳማ ከተማን ያስተናገደው ጅማ አባጅፋር 5-0 በማሸነፍ በመጣ ዓመት የፕሪሚየርሊጉ አሸናፊ ሆኗል። 

አጋራ
አጋራ

በጨዋታው ጅማ አባጅፋር ወላይታ ድቻ ጨዋታ የተጠቀመውን ሙሉ ለሙሉ በ4-4-2 አሰላለፍ  በጉዳት የራቀውን አሮን ከሞሀን በሔኖክ ኢሳያስ በመለወጥ የተጠቀመ ሲሆን በጨዋታውም በይሁንና አሚን የሚመራው የአባጅፋር የመሐል ክፍል ኳስን በሚገባ በመቆጣጠር የመጀመርያዎቹ 15 ደቂቃዎች የተዋበ እንቅስቃሴ የታየበት ሲሆን በተጨማሪም በርካታ የጎል ሙከራዎችም በኦኪኪ ተመስገንና ሔኖክ ኢሳያስ ማድረግ ችለዋል።  ደቂቃዎች እየገፉ በሄዱ ቁጥር የጅማ አባጅፋር ተጭኖ መጫወት እና የአዳማ ወደ ሃላ አፈግፍጎ መጫወትን ምርጫቸው አድርገው ነበር ፡፡

በኦኪኪና በተመስገን ፊት አውራሪነት የሚመራው የጅማ አባጅፋር የፊት መስመር የመጀመርያውን ጎል ለማስቆጠር የፈጀበት 9 ደቂቃ ነበር ከመሀል ከይሁን እንደሻው የተሻገረውን ኳስ ኦኪኪ በሚገባ ተቆጣጥሮት ተከላካይና በረኛውን በማለፍ የመጀመርያውን ጎል አስቆጥርዋል በዚች ጎል መቆጠር የተነቃቁት ጅማዎች ይበልጥ ጫና ሲፈጥሩ  አዳማ ከተማዎች ከኳስ ሃላ በመሆን በመከላከል በመልሶ ማጥቃት በዳዋ ሁቴሳ እንዲሁም  ከነአን ማርክነህ ከኮርና የተነሱ ኳሶች ቢሞክሩም ማስቆጠር አልቻሉም ይልቁንስ ጅማዎች ጫና በመፍጠር ተመስገን ከዮናስ የተሻገረችውን ኳስ በ36ኛ ደቂቃ ላይ በማስቆጠር የጅማን መሪነት ወደ ሁለት ከፍ አድርጎታል
ጫዋታው እየጋለ ሲሄድ ድንቅ የነበረው የአዳማ ከተማው በረኛ ጃኮ ፔንዜ ጉዳት አጋጥሞት ጫዋታውን መጨረስ ስላልቻለ ተቀይሮ ለመውጣት ተገዷል፡፡  በዚህ ጡዘት የቀጠለው  ጨዋታ ተጨማሪ ጎል ሳያስተናግድ በጅማ 2-0 መሪነት የመጀመርያው አጋማሽ ተጠናቋል።
አዲስ አበባ ላይ ካለው ሌላኛው ጨዋታ  ጋር በእኩል ሰዓት የጀመረው ይህ ጫዋታ አዲስ አበባ ላይ ካለው ጫዋታ ጋር እየተናበበ እንዳሄድ ይቆራረጥ ነበር 
ጅማዎች በሁለተኛው አጋማሽ  ይበልጥ ጫና ፈጥረው የተጫወቱ ሲሆን አዳማዎች ባንፃሩ አፈግፍገው  መጫወትን መርጠዋል በተደጋጋሚ በሄኖክ አዱኛና በኤልያስ አታሮ  ወደ ጎል የሚሻሙት ኳሶችን ወደ አጥቂዎቹ ተመስገንና እና ኦኪኪ  ሳይደረስ

 በአዳማው በረኛና ተከላካዮች ሲያመክኑ ውለዋል፡፡ በ58ኛው ደቂቃ ተመስገን ላይ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተሰጠውን ቅጣት ምት አዳማዎች ሳይዘጋጁ ተመስገን ለኦኪኪ በማቀበል ኦኪኪ ጫዋታውን ወደ 3ጎል ከፍ አድርጎታል ከዚህች ጎል በሃላም ይበልጥ ለማጥቃት ጅማዎች ይሁን  እንዳሻውን በንጋቱ ገብረስላሴ  በመቀየር ጫና ፈጥረው ተጭነው በማጫወት ኦኪኪ ድንቅ ሆኖ ባመሸበት ጨዋታ  66ኛ ደቂቃ ላይ ዮናስ ገረመው ያሻማውን ኳስ በመግጨት ሀትሪክ ሲሰራ ፣በ82ኛ ደቂቃ ላይ ለራሱ አራተኛ ለቡድኑ 5ኛ ጎል በማስቆጠር 5-0 ጅማ ማሸነፍ ችልዋል 

ጨዋታውም በጅማ አባጅፋር 5-0 አሸናፊነት መጠናቀቁን ተከትሎ በመጣበት ዓመት ዋንጫውን ማንሳት ችልዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...

መቐለ 70 እንደርታዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ዘርአይ ሙሉ በቴክኒክ አማካሪነት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሷል

አሰልጣኙን ያሰናበተው መቐለ 70 እንደርታ ሌላ ሹመትን ፈፅሟል። በያዝነዉ የዉድድር አመት ደካማ...