መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ በኢትዮጵያ እግር ኳስ አሻራውን በደማቁ ያሳረፈው አዳነ ግርማ ጫማውን ሊሰቅል ነው
ቅዱስ ጊዮርጊስወልቂጤ ከተማዜናዎች

በኢትዮጵያ እግር ኳስ አሻራውን በደማቁ ያሳረፈው አዳነ ግርማ ጫማውን ሊሰቅል ነው

አጋራ
አጋራ

በይስሐቅ በላይ

8 የፕሪሚየር ሊግ፣3 የአሸናፊዎች
አሸናፊ፣ 5 የሲቲ ካፕ፣4 የጥሎ ማለፍ
ዋንጫዎችን፣3 ጊዜ ደግሞ የሀገሪቱ ኮከብ
ተጨዋችነት ክብርን፣ በአጠቃላይ ከ20 በላይ
ዋንጫዎችንና ክብሮችን በመጎናፀፍ በኢትዮጵያ
እግር ኳስ አሻራውን በደማቁ ያሳረፈው አዳነ
ግርማ ጫማውን በመስቀል ራሱን ከእግር ኳስ
ዓለም ለማግለል እየተዘጋጀ መሆኑን በተለይ
ለሀትሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ገለፀ፡፡
በ1997 ዓ.ም ከሐዋሳ ፕሮጀክት ቡድን
ተነስቶ 15 የእግር ኳስ አመታትን ያሳለፈው
አዳነ ግርማ በውጤትና በድል የታጀበውን
ስኬታማ የእግር ኳስ ተጨዋችነት ህይወቱን
በያዝነው አመት መጨረሻ በክብር ለመቋጨት
መወሰኑንና በቀጣይም ራሱን በአሰልጣኝነት
ሙያ ለመፈተን መዘጋጀቱን በተለይ ለሀትሪክ
ገልጿል፡፡
ከ15 አመታት በላይ በዘለቀው የእግር ኳስ
ህይወቱ በተለይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ባሳለፈው
11 አመታት የቅዱስ ጊዮርጊስን ውጤታማነት
ከማስቀጠሉም በላይ የኢትዮጵያን እግር ኳስ
አንድ ደረጃ ከፍ በማድረጉ ታሪክ መቼም
ከማይዘነጋቸው ተጨዋቹ አንዱ የሆነው አዳነ
ግርማ በቅዱስ ጊዮርጊስና በኢትዮጵያ ብሔራዊ
ቡድን በሰጠው የረዥም አመት ስኬታማ
አገልግሎት ሁሌም ሲታወስበት የሚኖር ትልቅ
ሀውልት በብዙዎች ልብ ውስጥ ለመትከል
የበቃም ተጨዋች ነው፡፡
የያዝነው የውድድር አመት ሲጠናቀቅ
ራሱን ከክለብ ፉትቦል በይፋ ለማግለል
የመጨረሻ ውሳኔ ላይ የደረሰው አዳነ ግርማ
የረዥም አመት ስኬታማ የተጫዋችነት ህይወቱ
ያገኘውን እንዲሁም ከሀገር ውስጥና ከውጪ
አሰልጣኞች የቀሰመውን ልምዱን ከትምህርት
ጋር አጣምሮ የእግር ኳስ ተጨዋችነት
ስኬቱን በአሰልጣኝነት የመድገም ትልቅ ህልም
እንዳለው ለሀትሪክ ጨምሮ ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ብ/ቡድን ከ31 አመታት
ረዥም ትዕግስትና ቆይታ በኋላ ወደ አፍሪካ
ዋንጫ ከመለሱት ታሪክ ሁሌም ከሚያነሣቸው
ተጨዋቾች በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት
ተጨዋቾች አንዱ የሆነው አዳነ ግርማ
የኢትዮጵያ ብ/ቡድን ከ37 አመት በኋላ በአፍሪካ
ዋንጫ የውድድር መድረክ ላይ ብቸኛዋን ግብ
በማስቆጠር የራሱን ተጨማሪ ታሪክ ያፃፈም
ነው፡፡ አዳነ ግርማ ራሱን ከጨዋታ አለም
የማግለል ውሳኔውን ተከትሎ ለክለቡና ለሀገሩ
የሰጠው የማይዘነጋ ውለታን ግምት ውስጥ
በመክተት ስንብቱ ለአንድ ትልቅ ተጨዋች
የሚሰጠውን ክብር በሚመጥን መልኩ በክብር
መሰናበት እንዳለበት ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ
ይመሰክራሉ፡፡

(አዳነ ከሀትሪክ ጋር ያደረገውን
ሠፊ ቃለ-ምልልስ ሊንኩን በመጫን ይመልከቱ 👇

https://www.hatricksport.net/2019/11/21/%E1%8C%8A%E1%8B%AE%E1%88%AD%E1%8C%8A%E1%88%B5%E1%8A%95-%E1%8A%A5%E1%8B%88%E1%8B%B0%E1%8B%8B%E1%88%88%E1%8B%8D%E1%8D%A4-%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%8C%80%E1%88%98%E1%88%AA%E1%8B%AB-%E1%88%8D/

 

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታን ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ...