12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ቀጥለው ውለዋል።
አዲስ አበባ ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጫውተው ያለምንም ጎል አቻ ተለያይተዋል። ክልል ላይ ደግሞ ወልድያ ከተማ በአዲሱ ዘመናዊ ስታዲየም ሃዋሳ ከተማን አስተናግዶ 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል።
ከሜዳው ውጭ ወላይታ ዲቻን የገጠመው አዲስ አበባ ከተማ ደግሞ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 1 ለ 0፥ እንዲሁም አዳማ ላይ አዳማ ከተማ አርባ ምንጭ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
ጎንደር ላይ ደደቢትን ያስተናገደው ፋሲል ከተማ ደግሞ በደደቢት 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል። ድሬዳዋ ላይ የተደገረው የድሬዳዋ ከተማና የመከላከያ ጨዋታ አንድ እኩል በሆነ ውጤት ተጠናቋል። አዳማ ከተማ በ24 ነጥቦች ሲመራ ደደቢት በ23 እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በ21 ነጥቦች ይከተላል።
ነገ በ10 ሰዓት ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባቡናን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናግዳል;;

















አስተያየት ይስጡ