መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ዋልያዎቹ ከብላክስታሮቹ በኩማሲ ባባያራ ስታዲየም
ዋልያዎቹ

በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ዋልያዎቹ ከብላክስታሮቹ በኩማሲ ባባያራ ስታዲየም

አጋራ
አጋራ

 

  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ በካሜሩን አስተናጋጅነት
  • ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የጋና ብሔራዊ ቡድንን
  • ብላክስታሮችን በኩማሲው ባባያራ ስታዲየም ይፋለማል፤
  • ዋልያዎቹ በማጣሪያው ጨዋታ በምድባቸው ከጋና፣ ከሴራሊዮንና
  • ከኬኒያ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር የተደለደሉ ሲሆን ለእዚህም ወሳኝ
  • ጨዋታ ቡድኑ 22 ተጨዋቾችን በመያዝ ነው ወደ ስፍራው ሐሙስ
  • ዕለት ያመራው፡፡
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለእዚህ ወሳኝ ጨዋታም ልምምዱን
  • ከሌላው ጊዜ አኳያ ሰፋ ያለ ጊዜ ወስዶ ሲሰራ የከረመ ሲሆን
  • ለቡድኑም ከተመረጡት ተጨዋቾች መካከል በፕሮፌሽናል
  • ተጨዋችነት በግብፅ ሊግ የሚጫወቱት ሽመልስ በቀለና ኡመድ
  • ኡኩሪም ስኳዱን ተቀላቅለው ጠንካራ ልምምዳቸውን ከቡድኑ ጋር
  • ሲሰሩም ከርመዋል፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጋና ብሄራዊ
  • ቡድንን በጥሩ ሁኔታ ለመፋለም እና የራሱንም አቋም ለማወቅም
  • የአቋም መለኪያ ግጥሚያዎችንም ያደረገ ሲሆን
  • የመጀመሪያውንም ኢንተርናሽናል የአቋም መለኪያ ጨዋታውን
  • በሰርቢያዊው አሰልጣኝ ሚቾ ከሚመራው የኡጋንዳ ብሄራዊ ቡድን
  • ጋርም ባለፈው ሳምንት በሐዋሳው ኢንተርናሽናል ስቴድየም ላይ
  • በማድረግ 0-0 በሆነ ውጤትም ሊያጠናቅቅም ችሏል፡፡
  • በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመሩት የዋልያዎቹ ስብስብ
  • በእስካሁን የዝግጅት ጊዜያቸው ከመከላከያ ተስፋ ቡድንና ከፋሲል
  • ከተማ ቡድን ጋርም ያንን ያህል የቡድኑን አቋም የሚለካ
  • ባይሆንም የሟሟቂያ ግጥሚያም አድርገው 5-0 እና 3-0
  • ያሸነፉበት ግጥሚያ የሚጠቀስ ነው፣ ዋልያዎቹ ዛሬ ጋናን
  • ለሚፋለሙበት ጨዋታም ከግጥሚያው ጠንካራነት አንፃር እልህ
  • አስጨራሽ ፍልሚያ ይጠብቀዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ቡድኑ
  • ከሌሎች ጊዜ አጨዋወቶቹ አኳያ ለውጥ አድርጎ ከመጣ፣
  • መከላከሉ ላይ ብቻ ትኩረት ካላደረገ እና ኳስን ተቆጣጥሮና እንደ
  • ቡድን በመከላከል እና በማጥቃት ላይ አተኩሮ ከተጫወተ ጥሩ
  • ውጤት ይገጥመዋል ተብሎ እየተጠበቀም ነው፤ የኢትዮጵያ
  • ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ዕለት ከጋና ጋር በሚያደርገው
  • የመጀመሪያው ጨዋታ ለዋልያዎቹ መልካም ውጤት
  • እንዲገጥመው እንመኛለን፡፡
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዛሬን ጨዋታ በተመለከተ
  • በማጣሪያው ስለሚኖረን የማለፍ ዕድል የቡድኑ አሰልጣኝ አሸናፊ
  • በቀለን እና ከቡድኑ ተጨዋቾች መካከል አስቻለው ታመነን እና
  • አብዱልከሪም መሐመድን አናግረን ምላሻቸውን ሰጥተውናል፡፡
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ
  • ‘‘በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታው ማሸነፍ ብቻ አይደለም
  • ቢሳካልንና ዋንጫውን ብንበላስ ብለን ብናስብ መልካም ነገር
  • ነው”
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋናን ለሚፋለምበት የዛሬው የአፍሪካ
  • ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ የቅድመ ዝግጅቱን ሲሰራ ከርሟል፤
  • የወዳጅነት ጨዋታንም ከኡጋንዳ ጋር አድርጓል፤ ከእነዚህ
  • ዝግጅታችሁ ያገኛችሁት ጥቅም ምን ይመስላል?
  • ‘‘ለካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ያደረግነው ዝግጅት ጥሩ
  • የሚባል ነው፤ በቆይታችንም የቡድናችንን ተጨዋቾች አንድነት፣
  • ህብረት እንደዚሁም ደግሞ በግጥሚያው ላይ ጥሩ ውጤት
  • ለማምጣት የሚችሉበትን መነሳሳትና ከፍተኛ የመጫወት
  • ፍላጎትንም ልንመለከትበት ችለናል፤ የኡጋንዳ ብሄራዊ ቡድንን
  • በተፋለምንበት የአቋም መለኪያ ጨዋታ ላይ ደግሞ
  • የግጥሚያውን እድል ማግኘታችን ጠቀሜታው ጥሩ ነው፤ ያም
  • ሆኖ ግን አቋማችንን ሙሉ ለሙሉ ለማወቅ የቡድናችን
  • ተጨዋቾች የተጫወቱት 45 ደቂቃ ብቻ መሆኑ 90 ደቂቃው ምን
  • ይመስላል የሚለውን ለማየት እድለኞች አልሆንንም፤ ያም የራሱ
  • የሆነ ተፅህኖ አለው፤ እንደዛም ሆኖ ግን የኡጋንዳ ብሔራዊ
  • ቡድን በምስራቅ አፍሪካ ጠንካራ ከሆኑት አገራት መካከል አንዱ
  • ስለሆነ ከእነሱ ጋር የመጫወት እድል በማግኘታችን በእራሱ
  • ያለንበትን ሁኔታ በተወሰነ መልኩም ቢሆን እንድናይ አድርጎናል”፡፡
  • የኡጋንዳ ብሔራዊ ቡድንን ሐዋሳ ላይ በአቋም መለኪያ
  • ስትፋለሙ የነበራችሁ ክፍተትና ጠንካራው ጎን ምን ነበር?
  • ‘‘በወዳጅነት ጨዋታው ኡጋንዳን ስንገጥም በእኛ በኩል የነበረብን
  • ዋንኛ ችግር ግብ ማስቆጠሩ ላይ ነው፤ የአጨራረስ ችግራችን
  • ጎድቶናል፤ ይህ ችግር ደግሞ የሀገሪቱ የረጅም ጊዜ ክፍተትም
  • ሊሆን ችሏልና ይህን በፍጥነት ልናርመው ይገባል፡፡ በተቃራኒው
  • እኛ የነበረን ጠንካራ ጎን ደግሞ እንደህብረት የምንከላከልና
  • የምናጠቃ መሆኑ ነው፤ ይህንን ብቃት ይበልጥም አጠናክረን
  • ልናስቀጥለውም ተዘጋጅተንበታል”፡፡
  • የጋናን ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ለመለፋም ተዘጋጅታችኋል፤ ስለእነሱ
  • ወቅታዊ አቋም የቱን ያህል አውቃችኋል…. ከግጥሚያውስ ምን
  • ውጤትስ ለማምጣት ነው እያሰባችሁት ያላችሁት?
  • ‘‘የጋናን ብሔራዊ ቡድን ወቅታዊ አቋም በተመለከተ እነሱ
  • በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በዓለም እግር ኳስ ላይም እንዳላቸው
  • ጥንካሬ እውቅናና ብቃት ከተመለከትነው ነገር በመነሳት ብዙ
  • ነገሮችን አውቀናል፤ ያንንም ብቃታቸውንም በጋራ ማጥቃትና
  • በጋራ በመከላከልም በመጫወት ልንመከታቸውም ተዘጋጅተናል፡፡
  • የጋናን ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ስንገጥምም እኛ ወደሜዳ የምንገባው
  • ከግጥሚያው ጥሩ የሚባል ውጤትን ይዘን ለመውጣት ነው፤
  • ያንንም የማሳካት ብቃትም አለን፣ በጨዋታው ውጤታማም
  • እንሆናለን”፡፡
  • ዋልያዎቹን ለአፍሪካ ዋንጫ ከማሳለፍ ባሻገር ከምድቡም
  • እናልፋለን ብለህ ነበር፤ ይህንን እንዴት ተመለከትከው፤
  • የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ከጋና ጋር ስታነፃፅረውስ ዋልያዎቹን
  • በምን ደረጃ ላይ ታስቀምጣችኋለህ?
  • ‘‘የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ
  • ጨዋታዎቹ ላይ ግጥሚያዎቹን ማሸነፍ ብቻ አይደለም፤
  • ቢሳካልንና ዋንጫውን ብንበላስ፤ ስለዚህ አንድ ነገርን ለማሳካት
  • እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ መመኘትና ማሰብ መልካም ነገር
  • ነውና ውጤታማስ ለምን አይኮንም፤ አሁን ልጆቹ ያላቸው ፍላጎት
  • ጥሩ ነው፤ ከጋና ብሄራዊ ቡድን ጋር ስላለው ንፅፅር በሁለታችንም
  • መካከል ሰፊ ልዩነት አለን፤ ለንፅፅርም ያለንበት ስፍራም
  • አይመጥነንም፡፡ አሁን ባለን ትውልድም ከፍተኛ ለውጥ
  • እናመጣለን ማለትም ከባድ ነገር ነው፤ እታች መስራት
  • ያስፈልጋል፣ ላለንበት የእግር ኳስ ደረጃ ትኩረት ሊሰጥ
  • ያስፈልገዋል. ህዝብ ባለሙያና መንግስትም በጋራ በመሆን
  • የተቀናጀ ነገርም መስራት ያስፈልጋችኋል፡፡
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ አስቻለው ታመነ
  • ‘‘ከጋና ዛሬ ነጥብ ተጋርተን የምንመለስ ይመስለኛል”
  • ለካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ዛሬ ኩማሲ ላይ የመጀመሪያ
  • ጨዋታችሁን ታደርጋላችሁ፤ ስለዝግጅታችሁና ስለጨዋታው ምን
  • የምትለው ነገር አለ?
  • ‘‘የአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ህልማችንን ለማሳካት በዝግጅታችን
  • ወቅት በቴክኒክ፣ በታክቲክ እና በአህምሮአችን ላይ ጥሩ ነገርን
  • ሰርተናል፤ ከዚህ ዝግጅታችን ጎን ለጎንም የአቋም መለኪያ
  • ጨዋታንም ለማድረግ ችለናል፡፡ በጨዋታው ላይም ቡድኑ የራሱን
  • ጠንካራና ደካማ ጎንም ሊያይበትም ችሏልና በእዚህ መልኩ ነው
  • የተዘጋጀነው፤ ዝግጅታችንም ለጋናው ጨዋታ ብቻ ሳይሆን
  • ዋልያዎቹንም ወደ አፍሪካ ዋንጫውም ለማሳለፍ ስለሆነ ያንን
  • እልማችንንም የምናሳካውም ነው የሚሆነው፤ ስለዚህም
  • ቡድናችን ከዛሬው ጨዋታ ላይ እንደ እኔ እምነትም ከጋና ነጥብ
  • ተጋርተን የምንመለስም ይመስለኛል”፡፡
  • የጋናን ብሔራዊ ቡድን በተመለከተ የዛሬው ጨዋታ ላይ ስለእነሱ
  • ምን አይነት ግምትን ሰጥታችሁ ነው ወደሜዳ የምትገቡት?
  • ‘‘የጋና ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ አህጉር ላይ ብቻ ሳይሆን በአለም
  • ዋንጫም ላይ በመሳተፍ የሚታወቅ ትልቅ ቡድን እንደሆነ
  • ሁላችንም ነው የምናውቀው፤ እነሱንም ባላቸው ችሎታና ብቃትም
  • እናከብራችኋለን፤ እንጂ አንፈራቸውም፡፡ ጋና ትልቅ ቡድን ነው፤
  • ነገር ግን የእግር ኳስ ጨዋታ ሁሌም ራስህን በወቅታዊ እና በ90
  • ደቂቃም አቋምህም የምትለካበትና የምትመለከትበትም ስለሆነ
  • እኛም ያንን አስበን ነው የጋናን ጨዋታ የምናደርገው፡፡
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ አብዱልከሪም መሐመድ
  • ‘‘ጥሩ ስብስብ ስላለን ጋናን አሸንፈን አልያም ነጥብ ተጋርተን
  • ለመመለስ ነው የምንፈልገው”
  • የዋልያዎቹ ስብስብ ጋናን ዛሬ በአፍሪካ ዋንጫው የማጣሪያ
  • ጨዋታ ላይ ይፋለማሉ፤ ስለ ዝግጅታችሁ ስለተጋጣሚያችሁና
  • ስለግጥሚያው ምን ትላለህ…፡-
  • ‘‘የአፍሪካ ዋንጫው ማጣሪያ ዝግጅታችን ጥሩ የሚባል ነው፤
  • በመከላከልና በማጥቃቱም ላይ በምን መልኩ ማለትም ኳስ
  • ስናገኝና ስናጣ እንዴት መጫወት እንዳለብን ከልምምዳችን
  • በመነሳት እና በወዳጅነት ጨዋታውም ላይ ራሳችንን ለማሳየት
  • በመሞከር አቋማችንን በሚገባ ተመልክተናል፤ የጋናውን
  • ብላክስታር ወቅታዊ አቋም በተመለከተ ደግሞ እኛ ስለእነሱ
  • ከተመለከትነው ቪዲዬ በመነሳት ስለአጨዋወታቸው ያወቅነው
  • ነገር አለ፡፡ በጋራ ኳስን በማጥቃትና በመከላከል የሚጫወቱ
  • ናቸው፤ አግሬሲቭ ሆነውና ጠንከር ብለውም ነው የሚጫወቱት፤
  • እንደብዙዎች የአፍሪካ አገራትም የመስመር ላይ ኳስንም
  • ይጠቀማሉና እኛ ያንን አይተንም ነው እነሱን ለመግጠም
  • የተዘጋጀነው፤ ከጋና ጋር በሚኖረን ጨዋታ እኛ ወደ ሜዳ
  • የምንገባው ግጥሚያውን ለማሸነፍ ነው፤ ያ ካልተቻለ ነጥብ
  • ተጋርተን ለመምጣት ጥረትን የምናደርግ ይሆናል”፡፡
  • የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጋና፣ ከኬኒያ እና ከሴራሊዮን ጋር
  • ከመደልደሏ አኳያ ወደካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ታልፋለች?
  • ‘‘የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታው ላይ ምንም እንኳን በእኛ
  • ምድብ ጠንካራዋ ጋና ከእኛ ጋር ብትደለደልም አሁን ከያዝነው
  • ጥሩ የተጨዋቾች ስብስብ አኳያ እኛ ወደ ካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ
  • ለማለፍ ሰፊ እድል ነው ያለን፤ በመጀመሪያ በውድድሩ ተሳትፎ
  • ላይ ራሳችንን አንድ ነገር መስራት እንደምንችል ማሳመን አለብን፡፡
  • ለዚያም አዕምሮአችንን ማሳመን አለብን፡፡ ያንን ካደረግን
  • የምንፈልግበት ደረጃ ለይ የማንደርስበት ምንም አይነት ምክንያት
  • አይኖረንም”፡፡
አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...