መነሻ ገጽ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በኘሪሜየር ሊጉ ሲዳማና ደደቢት ሲያሸንፉ ኢትዮጵያ ቡና ድሬ ላይ ድል አልቀናውም
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በኘሪሜየር ሊጉ ሲዳማና ደደቢት ሲያሸንፉ ኢትዮጵያ ቡና ድሬ ላይ ድል አልቀናውም

አጋራ
አጋራ

PicsArt_1488459392107

በ22ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደደቢት እና ሲዳማ ቡና ሲያሸንፉ ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ በድሬዳዋ ከተማ ተሸንፏል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጭከወላይታ ድቻ ጋር ተጫውቶ 1 ለ 1 አቻ ተለያይቷል፡፡

ፈረሰኞቹ ከሜዳቸው ውጭ ነጥብ ተጋርተው ቢመለሱም በግብ ክፍያ በልጠው በ39 ነጥብ ሊጉን እየመሩ ይገኛሉ፡፡

received_1235843266496832

በአዲስአበባ ስታዲየም ቀደም ብሎ የተጀመረው ጨዋታ ደደቢት አዲስ አበባ ከተማን አስተናግዶ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ከሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በነጥብ ተስተካክሎ በጎል ክፍያ ተበልጦ  በ2ኛ ደረጃ ላይ ሊቀመጥ ችሏል፡፡

PicsArt_1491764434531-picsay PicsArt_1491764560256-picsay

በጨዋታው ጌታነህ ከበደ በ25ኛ እና በ27ኛ ደቂቃ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ሮበን ኦባማ በ30ኛ ደቂቃ ሶስተኛዋን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል፡፡

received_1190727437675082

ሲዳማ ቡና በበኩሉ ወልድያ ከተማን በይርጋለም ስታዲየም አስተናግዶ 2 ለ 1 አሸንፎ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ደደቢት እኩል 39 ነጥብ በመሰብሰብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ለሲዳማ ቡና ሙለዓለም መስፍን እና ላኪ ሳኒ፤ ለወልድያ ከተማ ደግሞ አንዱዓለም ንጉሴግቦችን አስቆጥረዋል፡፡

17861623_2267883443435925_1924175587018034998_n-1

ድሬ ላይ 10ሰዓት የጀመረው ከባድ ሙቀት የነበረበት  ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በድሬዳዋ ከተማ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል ለድሬዳዋ ከተማ በ2ኛው እና በ9ኛው ደቂቃ ላይ ሐብታሙ ወልዴ እዲሁም በ64ኛ ደቂቃ ዘነበ ከበደ ሲያስቆጥሩ ለኢትዮጵያ ቡና ከዜሮ ከመሸነፍ የዳነበትን ጎል መስኡድ መሀመድ አስቋጥሯል ፡፡

FB_IMG_1488737189738-660x400

ፋሲል ከነማ በአጼ ፋሲለደስ ስታዲየም ጅማ አባ ቡናን ያስተናገደበት ጨዋትም በፋሲል 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ለፋሲል ከነማ አብዱራህማን ሙባረክ እና ሙሉቀን ታሪኩ ግቦቹን ከመረብ ያሳረፉ ሲሆን የጂማ አባ ቡናን አንድ ግብ መሃመድ ናስር ነው ያስቆጠራት፡፡

received_1190728174341675

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ከሜዳው ውጭ አርባምንጭ ከተማን ገጥሞ በፒተር ኑዋድኬ እና በጂብሪል አህመድ ግቦች 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በፍፁም ገብረማርያም ሁለት ግቦች እና በኢብራሂም ፉፋ አንድ ተጨማሪ ግብ መከላከያን 3 ለ 0 ረትቷል፡፡

Adama-110x128hawassa

በአዳማ አበበ በቂላ ስታዲየም  አዳማ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ 2 ለ 2 አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

የደረጃ ሰንጠረዥ 

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

በዮሴፍ ከፈለኝ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...