“በሁለተኛው ዙር ጠንክረን በመምጣት ባለፈው ዓመት ያጣነውን የሻምፕዮንነት ክብር በማሳካት አዲስ ታሪክ እናፅፋለን” ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ)

በይስሐቅ በላይ

ደም ሲል የሠላም ሚኒስቴር
ከፍተኛ አመራሮችና በሠላም
ሚኒስቴር አማካይነት የተቋቋሙ
ሰላምን በሀገሪቱ ለማስፈን ሲሰለፉ ሲደክሙ
የነበሩት የሠላም እናቶች በጉልበታቸው
ተንበርክከው እንባዎቻቸው በሁለቱም
ጉንጮቻቸው የጎርፍ ያህል ፈሶበት እንኳን
ሙሉ ለሙሉ ሠላሙ ያልተመለሰለት
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ምክንያቱ በትክክል
ባልታወቀ ሁኔታ የአንደኛው ዙር ከመጠነኛ
ኮሽታዎች በስተቀር ፍፁም ሠላማዊ ሊባል
በሚችል መልኩ ተጠናክሮ ወደ ሁለተኛው
ዙር እየተንደረደረ ነው፡፡
በ120 ጨዋታዎች 279 ግቦች
ተቆጥረውበት አንደኛውን ዙር የሸኘው
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የፊታችን ቅዳሜና
እሁድ ከመጀመሩ በፊት ለዋንጫው አንገት
ለአንገት ከተናነቁ ክለቦች አንዱ የሆነው
የፋሲል ከነማና የኢትዮጵያ ብ/ቡድን ቁልፉ
ተጨዋች ሱራፌል ዳኛቸውን የሀትሪክ
ጋዜጣ ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር
ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ አንደኛው
ዙር እንዴት አለፈ? የውድድሩ ምርጥስ?
በሁለተኛው ዙር ግባችሁ ምንድነው? ሲል
ጠይቆታል፤በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ
ደምቀው እየበሩ ከሚገኙ ኮከቦች አንዱ
የሆነው ሱራፌል ዳኛቸው የአንደኛው
ዙር ትዝብቱን ከዚህ በታች ባለው መልኩ
ያጋራናል፡፡

አንደኛው ዙር ለፋሲልና  ለሱራፌል እንዴት ነበር?

“አንደኛው ዘር ለእኔም ለክለቦችም በጣም
ጥሩ ሆኖ ነው የተጠናቀቀው፤እኔ በግሌ ክለቤን
ውጤታማ ለማድረግ የማደርገው እንቅስቃሴ
የተሳካባትና ባደረኩት ነገርም ተደስቼበት
ያለፈ ነው፤ ክለቤ ፋሲልም እንደዚሁ
ውጤታማ የሆነበት መሪነቱን ተናንቆ
የጨረሰበት ነበር፤አምና በዚህን ጊዜ አንደኛው
ዙር ሲጠናቀቅ መሪ ከነበረው ከመቐለ 70
አንደርታ የ10 ነጥብ ልዩነት ነበረን…ዘንድሮ
ግን አንደኛው ዙር እስከተጠናቀቀበት ከመሪው
ቅ/ጊዮርጊስ ጋር ያለን የነጥብ ልዩነት 2 ነጥብ
ብቻ አንድ ጨዋታን በማሸነፍ ከሚገኝ ነጥብ
በታች ነው፤በዚህ መልኩ አንደኛውን ዙር
አጠናቀን መጨረሻችን እንደ መልካም ነገር
ነው የምወስደው፡፡

የአንደኛው ዙር ምርጡ ጨዋታና ውጤት?

“የአንደኛው ዙር ምርጡ ጨዋታ
የምለው ጅማ ላይ ከጅማ አባጅፋር ጋር
ያደረግነውና በአቻ ውጤት የተለያየንበት
ጨዋታ ነው፤ሙሉ ዘጠና ደቂቃውን
የጨዋታ ጊዜ የተቆጣጠርንበት…አሪፍ እግር
ኳስ የተጫወትንበት ለእኔ የአንደኛው ዙር
ምርጡ ጨዋታ ነበር ማለት እችላለሁ”

በአንደኛው ዙር በጣም የምትቆጭበት ጨዋታ?

“በቁጭት ደረጃ የማነሳቸው ማሸነፍ
ነበረብን የምላቸው ብዙ ጨዋታዎች አሉ፤
አሁን ለምሣሌ አዲስ አበባ ስታዲየም
ከሰበታ ጋር ተጫውተን ከ90ኛው ደቂቃ
በኋላ ግብ ተቆጥሮብን ነጥብ የተጋራንበት
ጨዋታ፣ ሀዋሳ ላይ ሀዋሳን 2ለ0 ስንመራ
ቆይተን ከኋላ ተነስተው ያሸነፉን ጨዋታ
በቁጭት ከማነሳቸው ጨዋታዎች በዋናነት
የምጠቅሳቸው ናቸው፤እነዚህን ጨዋታዎች
ማጣት የሌለብንን ነጥብ ያጣንባቸው ናቸው
ብዬ በቁጭት አነሳቸዋለሁ፡፡”

በአንደኛው ዙር በጣም የፈተነን ጠንካራ ቡድን
የምትለው?

“…እ…ኢት.ቡናና ቅ/ጊዮርጊስ…፤…
ከሁለቱም ቡድኖች ጋር ያደረግናቸው
ጨዋታዎች ቢፈትኑንም በተለይ ከቅ/
ጊዮርጊስ ጋር የነበረውን ጨዋታ
በሜዳችን ከተፈተንበት ጨዋታዎች
በዋናነት ይጠቀሳል፡፡ በሜዳችን ያደረግናቸ
ውን ጨዋታዎች በአንደኛው ዙር አሸንፈ
ናል ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ብቻ ነው ነጥብ
የተጋራነው፤ጊዮርጊሶችም በእለቱ በጣም
ፈትነውን ነበር… በተለይ ሲያጠቁ…ጫና
ሲፈጥሩ የተለዩ ነበሩና እነሱ ናቸው በጥንከ
ሬያቸው በአንደኛው ዙር በጣም የፈተኑን”

የአንደኛው ዙር ምርጡ ተጨዋች ማን
ነበር? ሱራፌል ራሱንም መምረጥ ይችላል?

“…ሣቅ…ራሴን እንኳን ራሴው ምርጥ
ነበር ብዬ አልመርጥም…(አሁንም ሣቅ)…
በአንደኛው ዙር ምርጥ ሊባሉ የሚችሉ
ተጨዋቾችን አይቻለሁ፤ ግን መምረጥ
ያለብኝ አንድ ተጨዋች
ስለሆነ ከነበሩት ምርጦች
ምርጥ መሆኑን በግብ
አ ይ ም ሬ ነ ቱ … ቡ ድ ኑ ን
በሚያስቆጥራቸው ግቦች
ወደ መሪነት ያንደረደረውን
ሙጂብ ቃሲምን ነው…
የአንደኛው ዙር ምርጥ
ብዬ የምመርጠው፤ ሙጅብ ቃሲም ያገኘውን
ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮ ቡድን ይዞ የሚወጣ
ተጨዋች በመሆኑ የምርጥነቱን ቅድሚያ
ሰጥቸዋለሁ”

በአንደኛው ዙር ያልተመቸህ?

“በአንደኛው ዙር ብዙ ነገሮች ጥሩ
ናቸው፤በጣም ብዙ ነገሮችም ተሻሽለዋል፣
ተስተካክለዋልም፡፡ በተለይ የስፖርታዊ
ጨዋነት ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ነው
የታየው፡፡ብዙ ነገሮች እንደተሻሻሉና እንደተ
ለወጡ ባልክድም ትንሽ ግን ዳኝነት ላይ
በተለይ የመስመር ዳኞች ላይ የሚታየው
ችግር በአንደኛው ዙር ምቾት ሳይሰጠኝ ነው
የተጠናቀቀው፡፡ በአንደኛው ዙር የመስመር
ዳኞች ፍትሀዊ ያልሆነ ስራን ሲሰሩ
አልፈዋል ከዋና ዳኛው ጋርም ለመግባባት
ሲቸገሩ ተስተውለዋልና በሁሉም ለማለት
ቢቸግረኝም በአንዳንዶቹ ግን አልተደሰትኩም፡
፡ በእርግጥ እኛ ተጨዋቾች ጋርም
ችግር የለም አልልም ችግር አለ…ግን…
ተሳስተሃል ልክ አይደለህም…ብለህ ስህተቱን
ለመንገር ስትል ጉዳዩን ወደ ሌላ በመውሰድ
ለስፖርታዊ ጨዋነት እንደማትገዛ የዳኛን
ውሳኔ የማታከብር አይነት አድርጎ ሊወስዱህ
ሲሞክሩ ይታያልና እዛ አካባቢ በአንደኛው
ዙር ችግር አይቻለሁና ይታረም፡፡”

በአንደኛው ዙር በቦታህ
አላንቀሳቅስ ብሎ ያስቸገረህ
ተጨዋች?

“በተናጠል ይሄ ነው ብዬ የምጠራው
ተጨዋች የለም፤ እንደውም ስለ ራሴ አካብጄ
ለማውራት ሣይሆን በጣም የተቸገርኩትና
በጣም የተማረርኩት እኔ ነኝ፡፡ ሁሌም
ከተቃራኒ ቡድን ጋር ስንጫወት የእኛን
ቡድን አጨዋወት ለማበላሸት ተብሎ
ማርክ (የምያዘው) የምደረገው እኔ
ነኝ፡፡ በጣም የሚገርምህ ደግሞ
ማርክ የምደረገው (የምያዘው) በአንድ
ተጨዋች ሣይሆን በሁለት በሶስት ተጨዋች
የምያዝበት ሁኔታ ነው ያለው፤ይህ ሁኔታ
እውነቴ ነው የምልህ በጣም አማሮኛል…
አንዳንዴ መዞር እስኪያቅተኝ ለሁለት ለሶስት
ወጥረው ነው የሚይዙኝ።ቡድኔ ውጤታማ
እንዲሆን የምፈልገውን እያደረኩ ብወጣም
በዚህ በኩል ግን እኔን ያስቸገረኝ ሣይሆን
የተቸገርኩት እኔው ራሴ ነኝ፡፡”

በሁለተኛው ዙር የፋሲልና የሱራፌል ግብ?

“ከእኔ የግል ክብርና ስኬት በላይ የክለቤን
ስኬትና ክብር አስበልጣለሁ…ከዚህ በመነሣት
የሁለተኛው ዙር ግባችን አንድና አንድ
የታወቀ ነው፤የሀገሪቱ ክለቦች የበላይ ሆኖ
የአመቱን ውድድር ማጠናቀቅ ነው ዋናው
ግባችን፤ ባለፈው አመት ለዚህ ክብርና ታሪክ
በጣም ተቃርበን በመጨረሻው ሰዓት ነው
እድሉን ያጣነው…ስለዚህ በሁለተኛው ዙር
የተሻለ ውጤት አስመዝግበን ባለፈው አመት
ያጣነውን የሻምፒዮናነት ክብርን ማሳካት
ነው ዋናው ግባችን፤ ደግሞም በእኛ ጥረት…
በእግዚብሔር እርዳታ በማሳካት አዲስ ታሪክ
እናፅፋለን ብዬ አስባለሁ”

በሁለተኛው ዙር ተሻሽሎ ባየው የምትለው ነገር?

“አብዛኛው ነገር በጣም ጥሩ ነው፤
በሜዳችን ስንጫወት…ወደ ሰው ሜዳም
ስንሄድ በአንደኛው ዙር የምታየው ነገር
በጣም ያስደስታል…ይሄ ነገር በሁለተኛው
ዙር ይበልጥ አድጎ ተሻሽሎ ባይ እግር ኳሱ
ፍፁም የሠላም መንደር ሆኖ ባይ ይበልጥ
እደሰታለሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ግን እንዳልኩህ
ጥሩ ዳኞች ስላሉ ሁሉንም በጅምላ መፈረጅ
ባልፈልግም በመካከላቸው ያሉ ዳኞች
በተለይ ደግሞ የመስመር ዳኞች በአንደኛው
ዙር የታየበባቸውን ድክመት አሻሽለው
ቢቀርቡ እላለሁ፤ ከዳኞች ውጪ እኛም
ተጨዋቾች ከውሳኔ ጋር የተያያዙ…በስሜት
የምናደርጋቸውን ነገሮች ቀንሰን በሁለተኛ
ዙር ብንቀርብ ብዬ ምክሬን እለግሳለሁ፤
ከዚህ በተረፈ በሁለተኛው ዙር ጥሩ ውድድር
የምናይበት ድል ግን በመጨረሻ ለፋሲል ብቻ
እንዲሆን ነው የምመኘው”

Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor.
The First Color Sport Newspaper in the country.

Yishak belay

Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor. The First Color Sport Newspaper in the country.