“በሁለተኛው ዙር ያለንን ነገር ሁሉ እንሰጣለን።” መሳይ ጳውሎስ /ሐዋሳ ከተማ/

በ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከታዩ ወጣት እና ድንቅ ተከላካዮች መካከል የሀዋሳ ከተማው መሳይ ጳውሎስ ይጠቀሳል። ክለቡ ሀዋሳ ከተማ ከመመራት ተነስቶ ፋሲል ከነማን ሲያሸንፍ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው ተከላካዩ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ከሀትሪክ ስፖርት ድረገፅ ሪፖርተር ከሆነው ቅዱስ ይምሩ ጋር አጠር ያለች ቆይታ አድርጓል። እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

ሀትሪክ፡ በቅድሚያ ለቃለ ምልልሱ ስለተባበርከን እናመሰግናለን። በመቀጠል እስኪ ስለ ዛሬው ጨዋታ እና የቡድኑ ስሜት ምን ይመስላል የሚለውን ብትነግረን

መሳይ፡ የቡድኑ ስሜት በጣም ድስ ይል ነበረ። ደጋፊውም እስከዛሬ ከነበረው በተሻለ ነበረ ሲደግፈን የነበረው። ደጋፊው ላይ ያለው ስሜት የራሱ ስሜት ነው። እኛ ሜዳ ውስጥ ያለውን ነገር ሰርተን ወጥተናል። እግዚአብሔር ይመስገን፤ ፈጣሪም ከኛ ጋራ ነበረ ብዬ አስባለሁ።

ሀትሪክ፡ ውጤቱ እንደታየው ከኋላ ተነስታችሁ ነው ማሸነፍ የቻላችሁት፤ አሰልጣኙም ይባረራሉ የሚል ጭምጭምታዎች ነበሩ፤ ከዚህ ባሻገርም ቡድኑ ውስጥ መከፋፈል አለ የሚባል ነገር አለና ይሄንን እንዴት ትገልፀዋለህ?

መሳይ፡ አዎ አኛም በወሬ ደረጃ ነው የምንሰማው፤ ዛሬ ሜዳ ውስጥ ያለውን ነገር መጨርስ እንዳለብን አምነን ነው የገባነው። ዛሬ የተቻለንን ሁሉ አድርገን የመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ ጨዋታ እንደመሆኑ መጠን የዛሬውን ጨዋታ ወስነን ነበር የመጣነው ፈጣሪ ይመስገን አሸንፈን ወጥተናል።

ሀትሪክ፡ ከመጀመሪያው ዙር አንፃር ሀዋሳ ከተማን በሁለተኛው ዙር እንዴት እንጠብቀው?

መሳይ፡ ሁለተኛ ዙር ላይ እኛ አይደለንም የምናውቀው፤ ፈጣሪ ነው የሚያውቀው። እኛ ያለንን ነገር ሁሉ እንሰጣለን። ከፈጣሪ ጋር ውጤቱን መጠበቅ ነው።

ሀትሪክ፡ በድጋሚ እናመሰግናለን። መልካም እድል።

መሳይ፡ እኔም በጣም አመሰግናለሁ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor