በሀገራዊ ስፖርት ሪፎርም ዙሪያ ለስፖርት ጋዜጠኞች ግንዛቤ ለመፍጠር የሚረዳ ውይይት በቢሾፍቱ ጀምሯል

በኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት በሀገራዊ የስፖርት ሪፎርም ዙሪያ ለስፖርት ጋዜጠኞች ግንዛቤ ለመፍጠር በቢሾፍቱ ቶሚ ኢንተርናሽናል ሆቴል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

 

በአሁን ሰዓት የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህር እና የስፖርት ሳይኮሎጂ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሳሙኤል ስለሺ የጥናታዊ ጽሁፍ ገለጻ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

በመቀጠል የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የስፖርት ሳይንስ መምህር እና የፊዚካል ፊትነስ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ዘር በቀለ ተጨማሪያ ጥናታዊ ጽሁፍ የሚያቀርቡ ይሆናል።

እንዲሁም የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን እቅድ እና በጀት ባለሙያ ለ10 ዓመታት የሚረዳ መነሻ የስፖርት ሪፎርም እቅድ የሚያቀርቡ ሲሆን፤ በመቀጠል አጠቃላይ ውይይት በቀረቡት ጽሁፎች ላይ ይካሄዳል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor