መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ​በሀገራችን ብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደ ተለመደው በነገው ማክሰኞ ነሀሴ 30/2009 ዕትሟ ከአዳዲስና ያልተሰሙ ዘገባዎች ጋር በእጅዎ
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ

​በሀገራችን ብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደ ተለመደው በነገው ማክሰኞ ነሀሴ 30/2009 ዕትሟ ከአዳዲስና ያልተሰሙ ዘገባዎች ጋር በእጅዎ

አጋራ
አጋራ

​በሀገራችን ብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ሀትሪክ
ስፖርት ጋዜጣ እንደ ተለመደው በነገው ማክሰኞ ነሀሴ
30/2009 ዕትሟ ከአዳዲስና ያልተሰሙ ዘገባዎች ጋር በእጅዎ
ልትገባ መሰናወዶዋን አጠናቅቃለች፡፡
– በሀገር ውስጥ የዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች
ማህበር (IAAF) እና የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ በላኩለት ግብዣ
መሰረት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ለመከታተል ወደ ለንደን
አምርቶ የነበረው የጋዜጣዋ ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሀቅ
በላይ የለንደን ቆይታውን ክፍል አንድ እንዳስነበበን ይታወሳል፡፡
በርካታ አንባቢዎቻችንም ክፍል ሁለትን ለማንበብ መጓጓታቸውን
ገልፀውልናል፡፡ በዚህም መሰረት ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ ቃሉን
ጠብቆ ክፍል ሁለት የለንደን ቆይታውን እነሆ ይዞልን ቀርቧል፡፡
በነገው ዕትሙም በግዙፉ የአርሰናሉ ኤምሬትስ ስቴዲየም ስለ
ነበረው አስደናቂ ጉብኝትና በስቴዲየሙ ታድሞ ስለ ተከታተለው
የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ እና ኤምሬትስ ምን ያህል አስደናቂ
ስቴዲየም እንደሆነ እጅግ በተዋቡ ቃላት በመሳጭ ሁኔታ
ይተርክልናል፡፡ ወደ ቼልሲው ስታምፎርድ ብሪጅም ጎራ ብሎ
ያወጋናል፡፡ ከዚህም ሌላ ስለ ለንደን ያልተሰሙ አስገራሚ
ዘገባዎችን ያደርሰናል፤ በጣም ይወዱታል፤ ይሄንን ገፅ ሳያነቡ
ወደ ሌሎቹ አያልፉም፡፡
– በአልባኒያ ሊግ ፕሮፌሽናል ተጨዋች የመሆን ዕድል ያገኘው
ቢንያም በላይ ካለበት አውሮፓ ሆኖ ከሀትሪክ ጋር ምርጥ ቃለ-
ምልልስ አድርጓል፤ ያንብቡት፡፡
– ከባህር ማዶ የሆንሪ ቃለ-ምልልስ፣ ስለ ድሪንክዎተር፣ ስለ
ዣቪ ሄርናንዴዝ፣ ስለ ኦዚል፣ ስለ ምባፔ ዝውውር፣ ስለ ዝውውር
መስኮቱ የመጨረሻ ቀን ድራማ እና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ
ምርጥ ምርጥ ዘገባዎች ቀርበዋል፤ ይደሰቱባቸዋል፡፡
– ነገ ማክሰኞ ነሀሴ 30/2009 ዓ.ም ለንባብ የምትበቃው
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡ ሌሎች
መረጃዎችንም በድረ-ገፃችን www.hatricksport.com
ማግኘት ይችላሉ፡፡ ነገ እንገናኝ፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...