በሀዋሳ ከተማ ውስጥ የሚገኙ አሰልጣኞች ለኮሮና ቫይረስ መከላከል የሚውል ድጋፍ አደረጉ።

ሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ከፕሮጀክት እስከ ፕሪሚየር ሊግ ያሉ አሰልጣኞች ለኮረና ቫይረስ ቅድመ መከላከል የሚውል የተለያዩ ለምግብ ግባአትነት የሚውል ቁሳቁሶችን ከራሳቸው እና ከከተማው በጎ ፍቃደኞች ባሰባሰቡት 45ሺ ብር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ ነው ቁሳቁሱን ያበረከቱት።

አሰልጣኞቹ በዋነኝነት ለጎዳና ተዳዳሪዎች እና ለአቅመ ደካሞች የሚውል የቁሳቁስ ድጋፍ ዛሬ በሀዋሳ ሚኒሊየም አዳራሽ በመገኘት ፓስታ፣ መኮሮኒ፣ ዱቄት፣ ዘይት እና ጨው የመሳሰሉትን ቁሳቁሶች ለሀዋሳ ከተማ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ እና በኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ በሚደረገው ድጋፍ የትምህርት፣ ጤና እና ስፖርት ኮሚቴ ሀላፊ ለሆኑት ለአቶ ደስታ ዳንኤል አበርክተዋል።