መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | ጅማ አባጅፋር ከቅ/ጊዮርጊስ
ቅዱስ ጊዮርጊስቅድመ ዳሰሳየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግጅማ አባጅፋር

ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | ጅማ አባጅፋር ከቅ/ጊዮርጊስ

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት 8ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ እና በቀጣዩ ሳምንት መጀመሪያ የሚካሄዱ ሲሆን ሁሉም ጨዋታዎች በክልል የሚደረጉ ይሆናል። ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል 6ቱ ጨዋታዎች ቅዳሜ ሲደረጉ እሁድ እና ሰኞ ደግሞ አንድ አንድ ጨዋታ የሚደረጉ ይሆናል። ከነዚህ ጨዋታዎች መካከል ጅማ ላይ ጅማ አባጅፋር ከቅ/ጊዮርጊስ የሚያደርጉትን ጨዋታ በዚህ ቅድመ ዳሰሳ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን አቅርበንላችኋል።

ጨዋታ
ጅማ አባጅፋር ከቅ/ጊዮርጊስ
የጨዋታ ቀን: ቅዳሜ ታህሳስ 18/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ኢንተርናሽናል አርቢትር ኃ/የሱስ ባዘዘው

ቅዳሜ ከሚደረጉት 6ጨዋታዎች መካከል በጅማ ስታዲየም ጅማ አባጅፋር ከቅ/ጊዮርጊስ የሚያደርጉት ጨዋታ 9:00 ላይ የሚጀምር ይሆናል። ወጥ አቋም ማሳየት የተሳነው የ14 ጊዜ የውድድሩ ሻምፒዮን ቅ/ጊዮርጊስ የውጤት መዋዠቅ ውስጥ ሆነው ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል። በቅ/ጊዮርጊስ በኩል እንደ መልካም ነገር ሊቆጠር የሚችለው ነገር የተከላካይ ክፍሉ ጥንካሬ ሲሆን በ4ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች እስካሁን ግብ ያልተቆጠረበት ብቸኛ ክለብ ቢያደርገውም የአጥቂ ስፍራው ደግሞ ድክመት እንዳለበት በሊጉ ያስቆጠረው ግብ 1ብቻ መሆኑ ግልፅ ማሳያ ነው። ተጋጣሚው ጅማ አባጅፋርም በውድድር ዓመቱ መጥፎ የሚባል ጊዜ እያሳለፈ ሲገኝ እስካሁን በሊጉ ድል ማስመዝገብ ካልቻሉ 3 ቡድኖች አንዱ ሊሆን ችሏል።

በ4ኛው ሳምንት ሁለቱም ቡድኖች ማሸነፍ የተሳናቸው ሲሆን ቅ/ጊዮርጊስ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ስሑል ሽረን አስተናግዶ ያለግብ አቻ ሲለያይ ጅማ አባጅፋርም ወደ መቐለ ተጉዞ የሊጉን መሪ ወልዋሎ አ.ዩ. ገጥሞ በተመሳሳይ ያለግብ አቻ ተለያይቶ የወልዋሎ አ.ዩ.ን የ100% የማሸነፍ ጉዞ ማምከን ችሏል። ሁለቱ ቡድኖች በ4ሳምንት የሊጉ ጉዞ በደረጃ ሰንጠረዡ በሶስት ነጥቦች ተበላልጠው ቅ/ጊዮርጊስ በ6 ነጥቦች 8ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ጅማ አባጅፋር ደግሞ በ3ነጥቦች 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...