መነሻ ገጽ አፍሪካ ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ / የቶታል ካፍ ኮንፌደሬሽን ካኘ  ወላይታ ዲቻ ከ ዛማሌክ
አፍሪካኮንፌድሬሽን ካፕወላይታ ድቻዜናዎችዳሰሳ

ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ / የቶታል ካፍ ኮንፌደሬሽን ካኘ  ወላይታ ዲቻ ከ ዛማሌክ

አጋራ
አጋራ

ዛሬ በአዲስ አበባ እና ሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲዬም ሀገራችን ወክለው በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግና የቶታል ካፍ ኮንፌደሬሺን ካፕ ቅድመ ማጣሪያ ለሚጫወቱት ቅዱስ ጊዬርጊስና ወላይታ ዲቻ  ጥሩ ውጤት እንዲገጥማቸው ሀትሪክ ስፖርት መልካም ምኞቷን ትገልፃለች፡፡

===================================

የቶታል ካፍ ኮንፌደሬሺን ካፕ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ትናንት  በተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች የተካሄዱ ሲሆን ዛሬም ቀጥለው  በተለያዩ ስታዲዬሞች ሲደረጉ፡፡

በቶታል ካፍ  ኮንፌደሬሺን ካፕ ኢትዮጵያን የወከለው ወላይታ ዲቻ በቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ በሜዳው የግብፁን ዛማሌክ በሳምንቱ አጋማሽ በዕለተ ዕሮብ ዛሬ ከቀኑ 10:00  ያስተናግዳል፡፡

  የ2009 ዓ/ም የኢትዮጵያ ክለቦች ጥሎ ማለፍ ዋንጫ  ሻምፒዬኑ  ወላይታ ዲቻ በክለቡ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሳተፍበት የቶታል ካፍ ኮንፌደሬሺን ካኘ፡ በመጀመሪያው የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ዛንዚባር አቅንቶ ከዚማሞቶ ጋር 1ለ1 በሆነ ውጤት ሲለያይ፡በሳምንቱ የመልስ ጨዋታ ዚማሞቶን በሜዳው ሀዋሳ ኢንተርናሺናል ስታዲዬም ያስተናገዱት የጦና ንቦቹ በጃኮ አረፋት የ27ኛ ደቂቃ የፍፁም ቅጣት ምት ብቸኛ ጎል በሜዳቸው 1ለ0 ተጋጣሚያቸውን በመርታት በድምር ውጤት  2ለ1 በማሸነፍ  ከዛማሌክ ጋር ወደሚያገናኛቸው ቀጣዩ  ማጣሪያ ማለፍ ችለዋል፡፡
የወላይታ ዲቻ ተጋጣሚ የሆነው የ5ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዬንስ ሊግ ሻምፒዬኑ የግብፁ ዛማሌክ ባለፈው አመት ሲካፈልበት ከነበረው ሻምፒዬንስ ሊግ ወርዶ ዘንድሮ ወደ ኮንፌደሬሺኑ ካኘ ሲመለስ በመጀመሪያው ዙር ቅድመ ማጣሪያ ሳያደርግ ፡የመጀመሪያውን ማጣሪያ በደርሶ መልስ ውጤት  አሸንፎ  ከመጣው ወላይታ ዲቻ ሲገናኝ፡ዛማሌክ በታሪክ ለ4ኛ ጊዜ ከኢትዮጵያ ክለቦች ጋር ሲገናኝ ከ2005 በሇላ የዛሬው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

ዛማሌክ ዘንድሮ በግብፅ ፕሪሚዬር ሊግ ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ ባይሆንም በቅርብ ጊዜያት መሻሻል እያሳየ ወደ አሸናፊነት እየተመለሰ ነው፡፡ዛማሌክ ከ5 የቅርብ ጨዋታዎች 5ቱንም በማሸነፍ ማግኘት ካለባቸው 15 ነጥብ 15ቱንም አግኝተዋል፡፡ቢሆንም በፕሪሚዬር ሊጉ ተቀናቃኙን  አልአህሊ መፎካከር አልቻለም፡፡ዛማሌክ ከአልአህሊ እኩል 27 ጨዋታዎችን አከናውኖ በደረጃ ሰንጠረዡ 2ኛ ላይ ቢቀመጥም በመካከላቸው ያለው የ21ነጥብ ልዩነት ስንመለከት ሻምፒዬኑ ከወዲሁ አልአህሊ ስለመሆኑ በርካቶችን ያስማማል፡፡

ባለሜዳዎቹ ወላይታ ዲቻዎች  በተመሳሳይ በፕሪሚዬር ሊጉ ወጥ አቋምን ማሳየት ተስኗቸው፡በሊጉ ወራጂ ቀጠና ቢቆዪም ከአሰልጣኝ ለውጥ በሇላ በትልቅ መነሳሳት ከወራጂ ቀጠና ወተው ተስፋ ሰጭ እንቅስቃሴ በማሳየት  ወደ አሸናፊነት እየተመለሱ ነው፡፡ 

በቅርብ ካደረጓቸው 5 የሊግ ጨዋታዎች 3ቱን አሸንፈው በ1 ተሸንፈው  በ1 አቻ ሲለያዩ  ማግኘት ከነበረባቸው 15 ነጥቦች 10 ነጥብ ማግኘታቸው  ስለ ዲቻ መሻሻል አንዱ ማሳያ ሲሆን  ፡፡ዚማሞቶን በደርሶ መልስ ማሸነፋቸው አሁንም ዛማሌክን ለማሸነፍ መነሳሳትን እንደፈጠረላቸው ተጨዋቾችና የቡድኑ አሰልጣኝ ዘነበ በላይ አሰተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በዛሬው ጨዋታ ባለሜዳዎቹ ወላይታ ዲቻዎች የዛንዚባሩን ዚማሞቶን ካሸነፉበት 11 ቋሚ ተሰላፊዎች አብዛኛዎቹ በመጀመሪያው አሰላለፍ ሲካተቱ ፡ዳግም ደስታ በጉዳት የማይሰለፍ ሲሆን እሱን ተክቶ አምረላ ደንሳታ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡ቡድኑ በ4-5-1 ፎርሜሺን ወደ ሜዳ እንደሚገቡ የሚጠበቅ ሲሆን ተጋጣሚያቸው ኳስን መስርተው እንዳይጫዎቱና ኳስ በዛማሌክ ተጫዋቾች እግር እንዳይቆይ የመሃል ተጨዋቾችን በቁጥር ማብዛቱ የተሻለ ነው፡፡

የጦና  ንቦቹ በዛሬው ጨዋታ ግብ እንዳይቆጠርበቸው በጥንቃቄ መጫዎትና ኳስን ይዘው ቶሎ ቶሎ ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል መድረስ ስህተት እንዲሰሩ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ የዛማሌክን ተሻጋሪ ኳሶች በህብረት መካከል ይኖርባቸዋል፡፡

ዛማሌክ አብዛኛውን ጊዜ በ4-3-3 ፎርሜሺን የሚጫዎት ሲሆን ቡድኑ ቀጥተኛ የማጥቃት አጨዋወትን የሚከተል ከመሆኑም፡በተጨማሪ በግራ እና ቀኝ መስመር በኩል ተሻጋሪ ኳሶችን ወደ ግብነት በመቀየር በኩል የተዋጣለት ሲሆን ቡድኑ ከቆሙ ኳሶችም የግብ ዕድል መፍጠር የሚችል ነው፡፡

ጨዋታውን በመሃል ዳኝነት ማሊያዊው ኤስማኤል ቺዚንጋ በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ካፍ አስታውቋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...