መነሻ ገጽ መቐለ ከተማ ቅድመ ዳሰሳ | ፋሲል ከተማ ከ ቅ/ጊዮርጊስ
መቐለ ከተማቅዱስ ጊዮርጊስቅድመ ዳሰሳወልዲያየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግፋሲል ከተማ

ቅድመ ዳሰሳ | ፋሲል ከተማ ከ ቅ/ጊዮርጊስ

አጋራ
አጋራ

የኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2ኛ ሳምንት አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ዛሬ(ረቡዕ) ጎንደር ላይ በአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።

በሁለተኛው ሳምንት መደረግ እያለበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን ውድድር ለነበረበት ማጣሪያ ዝግጅት እና ጨዋታዎች ምክንያት ሳይደረግ ቀርቶ ለዚህ ቀን የተላለፈው የፋሲል ከተማ እና የቅ/ጊዮርጊስ ጨዋታ ዛሬ(ረቡዕ) 9፡00 ሲል የሚደረግ ይሆናል።

በዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው ሲጫወት እየተቸገረ የሚገኘው ፋሲል ከተማ ዛሬ የሚያደርገው ጨዋታ 4ኛ የሜዳው ጨዋታ ይሆናል።(ከመቐለ ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ አ/አ ስታዲየም ላይ የተደረገ ነበር።) በ2009 የኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለቱን ቡድኖች ያገናኘው ጨዋታ ህዳር 25 ቀን 2009 ሲሆን በጨዋታውም ባለሜዳው ፋሲል ከተማ 2-1 በሆነ ውጤት ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

በ11ኛው ሳምንት የኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ አ/አ ስታዲየም ላይ ፋሲል ከተማ ከመቐለ ከተማ ጋር ተጫውተው ያለግብ አቻ የተለያዩ ሲሆን ቅ/ጊዮርጊስ በአንፃሩ ወደ ወልድያ ተጉዞ በተመሳሳይ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።

ፋሲል ከተማ በያዝነው የውድድር ዓመት በበርካታ ጨዋታዎች ላይ የሚጠቀመው 4-3-3 የጨዋታ ፎርሜሽንን ነው፡፡ ይህ ቡድን በአንዳንድ ጨዋታዎች ላይም 2 የተከላካይ አማካይን አጣምሮ ዘይቤውን ወደ 4-2-3-1 በመቀየር ሲጫወት ተስተውሏል፡፡ በዚህ የጨዋታ ዘይቤ ለቡድኑ ላቅ ያለ ግልጋሎትን እየሰጠ የሚገኘው ተጫዋች የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና አማካይ ዳዊት እስጢፋኖስ ነው። ተከላካዩ አብዱራህማን ሙባረክ(ግሪዳው) በቅጣት ያጣው ፋሲል ከተማ የተከላካይ ክፍሉ በፍጹም ከበደ፣ ሰኢድ ሀሰን፣ ከድር ሐረዲን እና አምሳሉ ጥላሁን የሚመራ ይሆናል። አጥቂው ራምኬል ሎክም የቀድሞ ቡድኑን የሚገጥም ይሆናል።

ቅ/ጊዮርጊስ በአንፃሩ 4-3-3 የጨዋታ ዘይቤን ይዞ ወደሜዳ እየገባ ይገኛል። አሁንም አጥቂዎቹን ሰልሀዲን ሰዒድ እና አሜ መሀመድን በጉዳት ያጣው ቅ/ጊዮርጊስ አቡበከር ሳኒን በሀሰተኛ ዘጠኝ ቁጥር ሚና አልፎ አልፎ ደግሞ አዲሱን ፈራሚ ሲዴ ኬታን በአጥቂነት እያጫወተ ይገኛል።

ፋሲል ከተማ በዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው 4ጨዋታዎችን ያከናወነ ሲሆን ወላይታ ድቻን በዓይናለም ኃይለ የ69ኛ ደቂቃ ብቸኛ ግብ 1-0 ያሸነፈበት ጨዋታ ብቸኛው በሜዳው ያስመዘገበው ውጤት ሲሆን ከወልዲያ ስፖርት ክለብ እና ከመቐለ ከተማ ጋር በተመሳሳይ 0-0 እንዲሁም ከሀዋሳ ከነማ ጋር 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።

ቅ/ጊዮርጊስ በአንፃሩ ማድረግ ከሚገባው 5 የሜዳው ውጪ ጨዋታዎች 4ቱን ያከናወነ ሲሆን ዛሬ ወደ ጎንደር ተጉዞ ከፋሲል ከተማ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ 5ኛው ይሆናል። ቅ/ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጪ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡናን በማሸነፍ አ/አ ላይ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር(ባለሜዳው ኢትዮጵያ ቡና ነበር።)፣ አዲግራት ላይ ከወልዋሎ አ.ዩ. ጋር እንዲሁም ወልድያ ላይ ከወልዲያ ከተማ ጋር ያለግብ 0-0 መለያየት ችሏል። ይህንን ተከትሎ ቅ/ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጪ ግብ ያላስተናገደ ክለብ ያደርገዋል።

በአጠቃላይ በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ማድረግ ከሚገባው 11ጨዋታዎች 9ጨዋታዎችን አድርጎ 4ጨዋታዎችን አሸንፎ 5ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት ፈጽሞ ያለምንም ሽንፈት ማግኘት ከሚገባው 27ነጥቦች 17ነጥቦችን ሰብስቦ ከመሪው ደደቢት በ8ነጥቦች ርቆ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ተጋጣሚው ፋሲል ከነማ በአንፃሩ 10 ጨዋታዎችን አድርጎ 3 አሸንፎ 7ጨዋታዎችን አቻ ወጥቶ ያለምንም ሽንፈት 16ነጥቦችን ሰብስቦ ከቅ/ጊዮርጊስ በ1 ነጥብ ዝቅ ብሎ 4ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡ ይህ ጨዋታም በአመቱ ሽንፈትን ባላስተናገዱ ሁለት ክለቦች መካከል የሚካሄድ ጨዋታ ይሆናል። ዛሬስ የትኛው ቡድን የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናግድ ይሆን? ወይንስ ጨዋታቸውን በአቻ ውጤት አጠናቀው ያለመሸነፍ ጉዟቸውን ያስቀጥላሉ? 9:00 ሲል የሚጀምረው ጨዋታ ምላሹን የሚሰጠን ይሆናል።

ከፋሲል ከተማ በኩል አይናለም ኃይሉ እና ይስሀቅ መኩሪያ በጉዳት እንዲሁም አብዱራህማን ሙባረክ(ግሪዳው) በቅጣት ምክንያት በዛሬው ጨዋታ የማይኖሩ ይሆናል። በቅ/ጊዮርጊስ በኩል ረጅም ጉዳት ላይ የሚገኙት ሳላዲን ሰዒድ፣ ናትናኤል ዘለቀ፣ አሜ መሃመድ፣ ታደለ መንገሻ እና አሉላ ግርማ ከጉዳታቸው ባለማገገማቸው በዚህ ጨዋታም የማይኖሩ ሲሆን የመስመር አጥቂው ጋዲሳ መብራቴ ልምምድ የጀመረ ቢሆንም ለጨዋታው መድረስ አለመድረሱ አጠራጣሪ ነው ተብሏል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ጎንደር አፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ላይ 9፡00 ሲል የሚጀምር ይሆናል።

በሌላ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ አ/አ ስታዲየም ላይ ወልድያ ስፖርት ክለብ ከ መቐለ ከተማ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። ይህ ጨዋታ በሊጉ 5ኛ ሳምንት ላይ መደረግ የነበረበት ቢሆንም በዕለቱ ወልድያ ላይ በተከሰተ የደጋፊዎች ፀብ እና ስርዓት አልበኝነት ምክንያት ሳይደረግ በመቅረቱ ለሌላ ጊዜ ተላልፎ የነበረው ጨዋታ ዛሬ በገለልተኛ ሜዳ አ/አ ስታዲየም ላይ የሚደረግ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ድንቅ የቅጣት ምቶች በነበሩት ጨዋታ ነገሌ ሲያሸንፍ ሀዋሳ በወልዋሎ ነጥብ ጥሏል

7 ጎሎች እና ሁለት ድንቅ የቅጣት ምት ጎሎች በነበሯቸው ሁለት ጨዋታዎች ነገሌ...