መነሻ ገጽ ቅድመ ዳሰሳ ቅድመ ዳሰሳ | ጅማ አባጅፋር ከ ወላይታ ድቻ
ቅድመ ዳሰሳወላይታ ድቻየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግጅማ አባጅፋር

ቅድመ ዳሰሳ | ጅማ አባጅፋር ከ ወላይታ ድቻ

አጋራ
አጋራ

 

ጨዋታ: ጅማ አባጂፋር ከ ወላይታ ዲቻ
የጨዋታ ቀን
የጨዋታ ቀን: ቅዳሜ ጥር 9/2012
የጨዋታ አርቢተር: ኢን አርቢተር ብሩክ የማነ ብርሀን
የጨዋታ ቦታ: ጅማ ዩኒቨርሲቲ ስታድዮም

ኮሽታ ሳይሰማበት በሰከነ መንፈስ 9ኛ ሳምንቱ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በነገው እለት (ቅዳሜ) በጅማ ዩኒቨርሲቲ ስታድዮም የካችአምና ቻምፕዮኖቹን ጅማ አባጂፋር እና በሊጉ በሜዳ እና ከሜዳ ውጪ ቀውሶች እየታመሱ የሚገኙትን እና በጊዚያዊ አሰልጣኛቸው ደለለኝ ደለቻ የሚመሩት ወላይታ ዲቻዎችን የሚያገናኝ ይሆናል።

በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮ በወላይታ ዲቻ አመራሮች ጠንከር ያሉ የተለያዩ ውሳኔዎች ሲወሰኑ የቆዩ ሲሆኑ ከውሳኔዎቹም በዋነኛነት ለመጥቀስ በክረምቱ ቡድኑን ከአሸናፊ በቀለ የተረከቡት አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ስንብት እና የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ሆሲሶ፣ ቴክኒካል ዳይሬክተሩ ታደሰ መታፈሪያና የደጋፊዎች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አንዷለም ከሀላፊነት መነሳት ይጠቀሳሉ፡፡

የክለቡ አመራር እርምጃ በአሰልጣኝ እና በአመራሮች ስንብት ብቻ ሳያበቃ ወደ ተጫዋቾችም ወርዶ ለ ሙባረክ ሽኩር: :ለአወል አብደላህ እና ለሳምሶን ቆልቻ የቡድኑ ውጤት መዋዥቅ አንዱ ምክንያት እናንተ ናቹ በማለት የማስጠንቀቅያ ደብዳቤ መስጠቱ ታውቋል።

በስተመጨረሻም የክለቡ አመራሮች እና የቡድኑ አባባላት ለክለቡ ውጤት መሳካት መስተካከል አሉባቸው ባልዋቸው ነጥቦች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል። ወላይታ ዲቻ በዚህ አመት ከስምንት ጨዋታ ስድስት ነጥብ አግኝቶ በሶስት የግብ እዳ በሊጉ ግርጌ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ወላይታ ዲቻን በሜዳው የሚያስተናግደው ጅማ አባጂፋር በአምስተኛው ሳምንት መርሀግብር ቅዱስ ጊዮርጊስን በጅማ ዩኒቨርስቲ ሜዳ ሁለት ለ አንድ ካሸነፈ በውላሃ ከአዳማ ከተማ ጋር ያለግብ አቻ ሲለያይ ባሳለፍነው ሳምንት ደግሞ ወደ አዲስ አበባ ተጉዞ ልምድ ያካበቱ ተጫዋቾችን ባሰባሰበው ሰበታ ከነማ 3 ለ አንድ በመሸነፍ በ ሊጉ 10 ነጥቦችን በመያዝ እና በአንድ የግብ እዳ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ነገ 9 ሰዓት በ ጅማ ዩኒቨርስቲ ስታድዮም ሁለቱም ክለቦች በተከታትይ ካጋጠማቸው የውጤት ማጣት ችግር ለመውጣት ከባድ ፍልሚያ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የ30ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች መናፍ ዐወል (አዳማ ከተማ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...