የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረጉ ሲሆን ነገ (አርብ) አንድ ጨዋታ የሚደረግ ሲሆን ከነገ በስቲያ (ቅዳሜ) ደግሞ ሰባት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል። በነገው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ስሑል ሽሬ ከ ፋሲል ከነማ የሚያደርጉትን ጨዋታ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን እንደሚከተለው ዳሰነዋል። መልካም ንባብ።
ጨዋታ: ድሬድዋ ከተማ ከ አዳማ ከተማ
የጨዋታ ቀን: ቅዳሜ ጥር 10/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ሄኖክ አክሊሉ
የጨዋታ ቦታ: ድሬድዋ ስታዲየም
ድሬድዋ ከተማ በአሰልጣኝ ስምኦን አባይ እየተመሩ ያለፉት የሊጉ ሁለት ጨዋታዎች ላይ ድል ማድረግ ባይችሉም በሊጉ አስፈሪ የፊት መስመር ያለውን ሲዳማ ቡና በደጋፊው ፊት ምሸነፍ ችለዋል ::
ድሬድዋ ከተማ በሊጉ አነስተኛ ግብ ካስቆጠሩ ክለቦች አንዱ ሲሆን ሰባት ግቦችን ብቻ ከተጋጣሚ መረብ ላይ ማሳረፍ ችለዋል ::
በመጀመሪያው አጋማሽ ሶስት ጎሎችን ሲያስቅጥሩ በሁለተኛው አጋማሽ ደግሞ ድግሞ አራት ግቦችን ከተጋጣሚ መረብ ላይ አሳርፈዋል::
አዳማ ከተማዎች ጥሩ ጅማሮን በሊጉ ቢያደርጉም የሃላ ሃላ በቀላሉ ነጥቦች እየጣሉ ለመሄድ ተገደዋል ::
በተለይም ከተጫዋቾች ደሞዝ ጋር በተያያዘ ቡድኑ ወደ ድሬድዋ ላይሄድ እንደሚችል ቢገለፅም ሀትሪክ ስፖርት ቅዳሜ ረፋዱን ለማጣራት እንደሞከረው ከሰአታት በፊት ድሬድዋ መግባታቸው ሲገለፅ መከፈል ከሚገባው የሶስት ወር ደሞዝ የመጀመሪያው እንደተከፈላቸው እና ቀሪ የሁለት ወር ክፍያ እንደሚቀር ተገልጿል::
ቡድኑ ጨዋታው በሚካሄድበት የድሬድዋ ስታዲየም ዝግጅት ሳያደርግ የሚያካሂደው ጨዋታ እንደመሆኑ ተጫዋችች በሜዳ ላይ የሚያሳዩት ነገር ከውዲሁ የሚጠበቅ ነው ::

አዳማ ከተማ በሊጉ ከድሬድዋ ባነሰ በሊጉ አነስተኛ ጎል ( አምስት )በማስቆጠር ቀዳሚው ክለብ ነው ::
አዳማ ከተማ በሊጉ ሁለተኛ ሳምንት ወልቂጤን ካሸነፈ በሃላ ባደረጋቸው ስድስት የሊጉ መርሀ ግብሮች ሶስት ነጥብ ማግኘት አልቻሉም ::
ድሬድዋ ከተማ በደጋፊዎቹ ፊት ድል የሚቀናው ከሆነ በደረጃ ሰንጠረዡ እስከ ዘጠነኛ መምጣት የሚችልበትን ሲያስመዘግብ አዳማዎች ድል የሚያደርጉ ከሆነ ከሉበት የአስራ ሁለተኛ ደረጃ ወደ ስድስተኛ የሌሎች ክለቦችን ውጤት ጠብቀው ከፍ ሊሉ የሚችሉበትን አጋጣሚ ሊፈጥሩ ይችላሉ ::
አስተያየት ይስጡ