ጨዋታ፡ ድሬዳዋ ከተማ ከወልዋሎ አ.ዩ.
የጨዋታ ቀን: ረቡዕ ታህሳስ 29/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ተካልኝ ለማ
ቦታ: ድሬደዋ ስታድየም
በ7ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ (ረቡዕ) 7ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን ከነዚህ መካከልም በድሬደዋ ስታዲየም ድሬደዋ ከተማ ወልዋሎ አ.ዩን የሚገጥምበት ጨዋታ አንዱ ነው።
መነሻቸው ከሁለቱ መስመሮች ባደረጉ ተሻሚ ኳሶች እድሎችን ለመፍጠር ሚሞክሩት ወልዋሎዎች በዛሬው ጨዋታ ተመሳሳይ የሆነ ጥንቃቄ የታከለበት አቀራረብ ይዘው ሊገቡ እንደሚችሉ ይገመታል። በሊጉ የመጀመርያ ጨዋታዎች ላይ ጥሩ አቋማቸውን ያሳዩት ወልዋሎዎች ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ማሸነፍ አለመቻላቸውን ተከትሎ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ግድ ሊላቸው እንደሚችል ይገመታል። ጥሩ መነሳሳት ላይ ሚገኙት ድሬዎች በበኩላቸው ጨዋታዎችን በሜዳቸው ማድረጋቸውን በግምት ሲገባ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወስደው በወጣቱ ያሬድ ታደሰና ጋናዊው ሬችሞንድ ኦዶንግ ላይ መሰረት አድርገው ለመጫወት ሊሞክሩ እንደሚችሉ ይገመታል።
ቢጫ ለባሾቹ ወልዋሎዎች ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር በነበረው ጨዋታ ጉዳት ያስተናገደውን አይናለም ሀይሉን ጨምሮ አቼምፖንግ አሞስ እና ካርሎስ ዳምጠውን በጉዳት ምክንያት ዛሬው ጨዋታ ውጪ ሲሆኑ፤ በደርቢው ጨዋታ በሁለት ቢጫ ከሜዳ የተሰናበተው ግብ ጠባቂው አብዱላዚዝ ኬይታ ቅጣቱን ጨርሶ ድሬዎችን ሚገጥም ይሆናል። ባሳለፍነው ሳምንት ከሜዳቸው ውጪ ጠንካራውን ሲዳማ ቡናን ያሸነፋት ድሬዎች በበኩላቸው አራት ተጨዋቾቻቸውን በጉዳት ያጣሉ። አንጋፋው አማካይ ምንያህል ተሾመ፣ አማኑኤል ተሾመ፣ ሳሙኤል ዘሪሁን እና በረከት ሳሙኤል ወልዋሎን ማይገጥሙ የብርቱካናማዎቹ ተጨዋቾች ናቸው።
አስተያየት ይስጡ