መነሻ ገጽ ስሁል ሽረ ቅድመ ዳሰሳ | ወላይታ ድቻ ከ ስሑል ሽረ
ስሁል ሽረቅድመ ዳሰሳወላይታ ድቻየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቅድመ ዳሰሳ | ወላይታ ድቻ ከ ስሑል ሽረ

አጋራ
አጋራ

ስምንተኛ ሳምንት ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዕለተ እሁድ 7 ጨዋታዎችን በሰባት ከተሞች ያካሂዳል።ሶዶ ስታድየም ላይ ሚካሄደው የወላይታ ድቻና ስሑል ሽረ ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል።

ጨዋታ: ወላይታ ድቻ ከ ስሑል ሽረ
የጨዋታ ቀን: እሁድ ጥሪ 2/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ተፈሪ አለባቸው
የጨዋታ ቦታ: ሶዶ ስታድየም

በገብረክርስቶስ ቢራራ ሚመሩት የጦና ንቦች መኳኳንንት አሸናፊ፣ያሬድ ዳዊት እና ነጋሽ ታደሰን በጉዳት ሲያጡ ስሑል ሽረዎች በበኩላቸው በ7ተኛው ሳምንት ከሰበታ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ ጉዳት ያስተናገደው ተከላካዩ አዳሙ ማሳላቺ ና ግብ ጠባቂው ወንድወሰን አሸናፊን በጉዳት አያሰልፋም።

የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ላይ መሰረት ያደረገ አጨዋወትን ሚከተሉት ወላይታ ድቻዎች ነገም ተመሳሳይ አቀራረብን ይዘው ወደ ሜዳ ሊገቡ እንደሚችሉ ይገመታል።መሀል ላይ ሚሰለፋትና የቡድኑን ቅርፅ ከኃላ ሆነው ሚመሩት ተስፋዬ አለባቸውና በረከት ተስፋዬ ከሜዳቸው ውጪ ወደ ኃላ አፈግፍገው ሚጫወቱትን ስሑል ሽረዎችን ለማስከፈት የተመጠኑ ኳሶችን ወደ መስመር በመበተን ሜዳውን በማስፋት ክፍተቶችን ለማግኘት ይሞክራሉ ተብሎ ይገመታል።በተጨማሪም መስመር ላይ ሚሰለፋት ዳንኤል ዳዊት ና ቸርነት ጉግሳ ከፈጣኑ ባዬ ገዛሀኝ ጋር በመጣመር የተመጠኑ ኳሶች በማድረስ የጠሩ የግብ እድሎች እንዲፈጠሩ ማድረግ ግድ ሚላቸው ይሆናል።

መስመር ላይ መሰረት ያደረገ መልሶ ማጥቃትን ምርጫጨውን ሚያደርጉት ስሑል ሽረዎች ነገም በተመሳሳይ ወደ ኃላ አፈግፍገው በዲድዬ ሌብሪና አብዱልለጢፍ መሐመድ አማካኝነት እድሎችን ለማግኘት ይሞክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።በቅርብ ጨዋታዎች እየተሰለፈ ለተከላካይ ክፍሉ በቂ ሽፋን በመስጠትና ኳሶችን በማጨናገፍ መሀል ላይ የቡድኑ ቁልፍ ተጨዋች እየሆነ ያለው ነፃነት ገብረመድህን ከሀብታሙ ሸዋለም እና ሙሉአለም ረጋሳ ጋር ሚኖራቸው ጥምረት ቡድኑ ከመከላከል ወደ ማጥቃት እንዲሁም ከማጥቃት ወደ መከላከል በሚኖረው ሽግግር ላይ ከፍተኛ ድርሻ ሚኖራቸው ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የ30ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች መናፍ ዐወል (አዳማ ከተማ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...