መነሻ ገጽ ቅድመ ዳሰሳ ቅድመ ዳሰሳ | ወላይታ ድቻ ከፋሲል ከነማ
ቅድመ ዳሰሳወላይታ ድቻየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግፋሲል ከተማ

ቅድመ ዳሰሳ | ወላይታ ድቻ ከፋሲል ከነማ

አጋራ
አጋራ

ጨዋታ: ወላይታ ድቻ ከ ፋሲል ከነማ
የጨዋታ ቀን: ረቡዕ ታህሳስ 29/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ሃብታሙ መንግስቴ
ቦታ: ወላይታ ድቻ ስታዲየም

7ተኛ ሳምንት ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በበዓል ቀን እና ከበዓል ማግስት በሚካሄዱ ስምንት ጨዋታዎች ቀጥሎ ይካሄዳል።

ባሳለፍነው ሳምንት የስድስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመንትዮቹ (በወንድማማቾች) ደርቢ ላይ ጣፋጭ ድል በማስመዝገብ የሊጉ መሪ መሆን የቻሉት አፄዎች ከሜዳቸው ውጪ የመጀመሪያ ሶስት ነጥብ ለማግኘት የሚያደርጉት ትልቅ ጨዋታ እንደሚሆን ይጠበቃል።

አፄዎቹ በሊጉ ከሜዳቸው ውጪ ባደረጉት ሶስት ጨዋታዎች በሁለቱ ሲሸነፉ በአንዱ አቻ መውጣት ችለዋል።

ወላይታ ድቻዎች ከሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት በደቡብ ደርቢ ሲዳማ ቡናን ካሸነፉ በኋላ ሶስት ነጥብ በሜዳቸውም ሆነ ከሜዳቸው ውጪ ማግኘት ተስኗቸው ታይቷል። ካደረጎቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ማሳካት አቅቷቸው ሲስተዋል በሶስት ጨዋታዎች ተሸንፈው በሁለቱ ጨዋታዎች አቻ መለያየት ችለዋል።

በአሰልጣኝ ገብረ ክርስቶስ ደስታ የሚመሩት ወላይታ ዲቻዎች በሊጉ አስፈሪ እና ጠንካራ የፊት መስመር ባለው የፋሲል ከነማ ቡድን እንደሚፈተን ይጠበቃል።

በጨዋታው ልዩ ክስተት ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ሶስቱ ወንድማማቾች በሁለቱ ክለብ የሚገናኙበት አጋጣሚ ነው። ሽመክት ጉግሳ ፋሲል ከነማን ወክሎ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ሲጠበቅ ቸርነት ጉግሳ እና አንተነህ ጉግሳ በወላይታ ድቻ በኩል ሊሰለፉ እንደሚችል ይጠበቃል።

በአንጋፋው ደጉ ደበበ የሚመራው የወላይታ ድቻ የተከላካይ ክፍል ትልቅ ፈተና እንደሚጠብቀው ከወዲሁ መላ ምቶች እየተሰጡ ይገኛሉ።

ሁለቱ ቡድኖች በባለፈው የውድድር አመት በመጀመሪያው ዙር ጥር 11 ሲገናኙ ጨዋታቸውን ማድረግ የቻሉት በአዲስ አባባ ስታዲየም ነበር። ጨዋታውን ፋሲል ከነማዎች በያሬድ ባዬ የፍፁም ቅጣት ምት ጎል ማሸነፋቸው ይታወሳል።

ፋሲል ከነማ በጨዋታው ድል የሚቀናው ከሆነ መሪነቱን ሲያጠናክር በሌላ በኩል ደግሞ ወላይታ ድቻዎች በደጋፊዎቻቸው ፊት ድልን የሚቀናጁ ከሆነ የሌሎች ቡድኖች ነጥብን ጠብቀው እስከ ሰባተኛ ደረጃ ሊቆናጠጡ የሚችሉበትን እድል ይፈጥራሉ።

ያሬድ ባዬህ እና እንየው ካሳሁን አሁንም በጉዳት ለፋሲል ከተማ ግልጋሎት የማይሰጡ ሲሆን ወላይታ ድቻ ከጉዳት የፀዳ ስብስብ ይዘው ለዛሬው ጨዋታ ወደ ሜዳ ይገባሉ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...