የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረጉ ሲሆን ትናንት (ቅዳሜ) አንድ ጨዋታ የተደረገ ሲሆን ዛሬ (እሁድ) ደግሞ ሰባት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል። በዛሬው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል አዳማ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ የሚያደርጉትን ጨዋታ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን እንደሚከተለው ዳሰነዋል። መልካም ንባብ።
ጨዋታ: አዳማ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ
የጨዋታ ቀን: እሁድ ጥር 03/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ
የጨዋታ ቦታ: አዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም
በሰባተኛው ሳምንት ወደ መቐለ አቅንተው በመቐለ 70እንድርታ 2-0 ሽንፈትን ያስተናገዱት በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመሩት አዳማ ከተማዎች በሜዳቸው ሀዋሳ ከተማን ያስተናግዳሉ። በሜዳቸው ከወልቂጤ ከተማ ካስመዘገቡት ሶስት ነጥብ ውጪ አብዛኛውን ጨዋታ በአቻ ውጤት ያጠናቀቁት አዳማዎች በሊጉ በ8ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ቡድኑ ከሌሎች ያልተቀየረ ስብስብ ቢኖረውም በማጥቃት ረገድ ተጋጣሚውን ቡድን ከማስጨነቅ ባሻገር ጎል የማስቆጠር ችግር ይታይበታል። በዛሬው ጨዋታ ቡሩክ ቃልቦሬን እና ሚካኤል ጆርጅን በጉዳት የማይጠቀምባቸው ሲሆን መጠነኛ ጉዳት ገጥሞት የነበረው አዲስ ህንጻም መሰለፉ አጠራጣሪ ሆኗል። ይበልጥ ፈጣን የማጥቃት ስትራቴጂ ይዞ ይገባል ተብሎም ይገመታል።
በሊጉ ወጥ አቋም ማሳየት የተሳኛቸው የሚመስሉት የአሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ሀዋሳ ከተማዎች ከሜዳቸው ውጪ አዳማ ከተማን ይገጥማሉ። በኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም በሲዳማ ቡና በሰፊ ጎል ሽንፈትን ካስተናገዱ በኳላ ተከታታይ ጨዋታቸውን በአቻ ውጤት አጠናቀዋል። የሳሳ የመሀል ሜዳ እና የተከላካዮች መዘናጋት ችግር ይስተዋልበት የነበረው 7ኛው ሳምንት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በሜዳቸው ባደረጉት ጨዋታ በተወሰነ መልኩ መሻሻል ታይቶበታል። ወሳኝ አጥቂያቸውን መስፍን ታፈሰን በጉዳት የማገኙት እና ባለፈው ሳምንት ከጉዳት ተመልሶ የነበረው የእስራኤል እሸቱም መሰለፉ አጠራጣሪ ሆኗል። ሀዋሳዎች የአዳማዎችን የተከላካይ መስመር በቡሩክ በየነ እና በእስራኤል እሸቱ ጥምረት ይፈተናሉ ተብሎ ይገመታል። ሁለቱ ቡድኖች እስካሁን በባደረጉት 37 የእርስ በእርስ ግንኙነት ሀዋሳዎች 18ጊዜ በማሸነፍ ቀዳሚ ሲሆኑ አዳማዎች 8ጊዜ ብቻ ማሸነፍ ችሏል።
ግምታዊ አሰላለፍ
አዳማ ከተማ
ጃኮ ፔንዜ
ስሌማን ሰሚድ – ምኞች ደበበ -ቴዎድሮስ በቀለ – ስሌማን መሀመድ
አዲስ ህንፃ -አማኑኤል ጎበና -ከነአን ማርክነህ
በረከት ደስታ- ዳዋ ሆቴሳ – ቡልቻ ሹራ
ሀዋሳ ከተማ
ቤሊንጋ ኢኖህ
ዳንሌል ደርቤ- መሳይ ፃውሎስ- ላውረንስ ላርቴ -ኩዋሜ ኦሊቨር
አክሊሉ ተፈራ- ተስፋዬ መላኩ -አለልኝ አዘነ- ሄኖክ ድልቢ
ብሩክ በየነ – ሄኖክ አየለ
አስተያየት ይስጡ