የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረጉ ሲሆን ዛሬ (አርብ) አንድ ጨዋታ የተደረገ ሲሆን ነገ (ቅዳሜ) ደግሞ ሰባት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል። በነገው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ባህርዳር ከተማ ከወልዋሎ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን እንደሚከተለው ዳሰነዋል። መልካም ንባብ።
ጨዋታ: ባህርዳር ከተማ ከ ወልዋሎ
የጨዋታ ቀን: ቅዳሜ ጥር 09/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ኢንተ አርቢትር ለሚ ንጉሴ
የጨዋታ ቦታ: ባህርዳር ስታዲየም
መሀላቸው ላይ የ3 ነጥብ ልዩነት ይዘው ሚገናኙት ሁለቱም ክለቦች ባሳለፍነው ሳምንት ከደረሰባቸው ሽንፈት ለማገገም ከፍተኛ ፋክክር ያለበት ጨዋታ ያሳያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
እስካሁን በሜዳቸው ባደረግዋቸው 3 ጨዋታዎች ላይ ያልተሸነፋት የጣና ሞገዶቹ በሜዳቸው ሲጫወቱ የሚጠቀሙትን ማጥቃት ላይ መሰረት ያደረግ አጨዋወታቸውን ነገም ወደ ሜዳ ለመተግበር ይሞክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።ባህርዳር ከተማዎች ከሜዳው ውጪ ሲጫወት ጥብቅ መከላከልን ለመተግበር ሚሞክረውን ወልዋሎን ለማስከፈት የሜዳውን ስፋት በመስመር ተጨዋቾቻቸው መጠቀም ግድ ይላቸዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት በሜዳቸው በሀድያ ሆሳእና ሽንፈት ያስተናገዱት ቢጫ ለባሾቹ ከመሪዎቹ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ የግድ ከነገው ጨዋታ ነጥብ መያዝ አለባቸው።አስገራሚ አጀማመራቸውን ማስቀጠል ያልቻሉት ወልዋሎዎች በነገው ጨዋታ መልሶ ማጥቃት ላይ ትኩረት ያደረገ የማጥቃት ዘዴ ይዘው ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።በተለይ መስመር ላይ መሰረት ያደረገውን የባህርዳሮችን የማጥቃት እንቅስቃሴን መመከት ላይ ከፍተኛ ስራ ይጠበቅባቸዋል።
ባህርዳሮች በሜዳቸው ባደረግዋቸው 3 ጨዋታዎች ላይ 10 ግቦችን ሲያስቆጥሩ 5 ግቦችን አስተናግደዋል፤ወልዋሎዎች በበኩላቸው ከሜዳቸው ውጪ 4 ጨዋታዎችን አድርገው 8 ግቦችን ሲያስቆጥሩ 2 ግቦችን አስተናግደዋል።
በነገው ጨዋታ ባህርዳሮች ወሰኑ ዓሊና አቤል ውዱን በጉዳት ሲያጡ፣የኮከብ ተጨዋቻቸውን ፍፁም ዓለሙን ማሰለፋቸው አጠራጣሪ ሆንዋል።
አይናለም ሀይሉ ና ካርሎስ ዳምጠው በወልዋሎዎች በጉዳት ለነ ማይደርሱ ተጨዋቾች ናቸው።በ3ኛው ሳምንት ከስሑል ሽረ ጋር በነበረው ጨዋታ ጉዳት ያስተናገድው አቼምፖንግ አሞስ ከጉዳቱ አገግሞ ለነገው ጨዋታ ይደርሳል።
አስተያየት ይስጡ