የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረጉ ሲሆን ነገ (አርብ) አንድ ጨዋታ የሚደረግ ሲሆን ከነገ በስቲያ (ቅዳሜ) ደግሞ ሰባት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል። በነገው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ስሑል ሽሬ ከ ፋሲል ከነማ የሚያደርጉትን ጨዋታ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን እንደሚከተለው ዳሰነዋል። መልካም ንባብ።
ጨዋታ: ስሑል ሽሬ ከ ፋሲል ከነማ
የጨዋታ ቀን: አርብ ጥር 09/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር:
የጨዋታ ቦታ: ትግራይ ስታዲየም
ስሑል ሽሬ በሊጉ በሶስተኛው ሳምንት በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ከደረሰበት ሽንፈት በኋላ በሊጉ አስደናቂን ጉዞ በማድረግ ከተጋጣሚው ፋሲል ከነማ በእኩል አስራ ሁለት ነጥብ በጎል ክፍያ ተበልጦ አምስተኛ ላይ ተቀምጠዋል ::
- ማሰታውቂያ -
ፋሲል ከነማዎች በሜዳቸው በሊጉ ካልተሸነፉ ክለቦች አንዱ ሲሆኑ በሜዳቸው ከተሸነፉም አመታት ተቆጥረዋል :: ይህ ጥንካሬያቸው ግን ከሜዳቸው ውጪ ባሉ ጨዋታዎች ላይ እየታየ አይገኝም ::
ፋሲል ከነማዎች በዘንድሮው አመት የሊጉ ጉዞ ከሜዳቸው ውጪ ማሸነፍ ተስኖቸው ታይቷል ::
ፋሲል ከነማ በሊጉ የተጋጣሚ መረብ ላይ በአጠቃላይ 17 ጎሎችን በማስቆጠር ቀዳሚው ክለብ ነው :: ካስቆጠራቸው 17 ጎሎች መካከል ደግሞ 13 ጎሎች በሁለተኛው አጋማሽ የተቆጠሩ ናቸው ::
ስሑል ሽሬ በሌላ በኩል በሊጉ 6 ጎሎችን ብቻ በማስቆጠር አነስተኛ የግብ መጠን ካስቆጠሩ ክለቦች መካከል አንደኛው ናቸው :: ካስቆጠሩት ስድስት ጎሎች መካከል ደግሞ በመጀመሪያው አጋማሽ ብቻ አራት ጎሎችን ማስቆጠር ችለዋል ::
ስሑል ሽረ በጉዳት ሆነ በቅጣት የሚያጡት ተጨዋች አይኖርም ፤ ከሰበታ ጋር በነበረው ጨዋታ ጉዳት ያጋጠመው አዳም ማሳላቺ ተመልሷል።
ፋሲል ከነማ ጉዳት ላይ የነበሩት ያሬድ ባዬ ፣ እንየው ካሳሁን ፣ ሀብቴ እና ሙባረክ(ግሪዳው) ወደ ልምምድ ቢመለሱም ለነገው ጨዋታ አይደርሱም።
ፋሲል ከነማ ጉዳት ላይ የነበሩት ያሬድ ባዬ፣እንየው ካሳሁን፣ሰለሞን ሀብቴ ና አብዱራህማን ሙባረክ(ግሪዳው) ወደ ልምምድ ቢለሱም ለነገው ጨዋታ አይደርሱም።
የሁለቱ ቡድኖች መርሀ ግብር ከወዲሁ በጉጉት ሲጠበቅ የጨዋታው አሸናፊ የሌሎች ቡድኖችን ውጤት ጠብቆ የሊጉ መሪ የሚሆንበትን እድል ይፈጥራል ::