መነሻ ገጽ መቐለ 70 እንደርታ ቅድመ ዳሰሳ | መቐለ 70 እንደርታ ከ ሰበታ ከተማ
መቐለ 70 እንደርታሰበታ ከተማቅድመ ዳሰሳየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቅድመ ዳሰሳ | መቐለ 70 እንደርታ ከ ሰበታ ከተማ

አጋራ
አጋራ

 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረጉ ሲሆን ዛሬ (አርብ) አንድ ጨዋታ የተደረገ ሲሆን ነገ (ቅዳሜ) ደግሞ ሰባት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል። በነገው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል መቐለ 70 እንደርታ ከሰበታ ከተማ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን እንደሚከተለው ዳሰነዋል። መልካም ንባብ።

ጨዋታ: መቐለ 70 እንደርታ ከ ሰበታ ከተማ
የጨዋታ ቀን: ቅዳሜ ጥር 09/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ሀብታሙ መንስቴ
የጨዋታ ቦታ: ትግራይ ስታዲየም

ትግራይ ስታድየም የሳምንቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መሪ መቐለ 70 እንደርታና ሰበታ ከተማን ጨዋታ ነገ ከቀኑ 9 ሰዓት ሲል ያስተናግዳል።ተከታታይ ሁለት ጨዋታዎችን በማሸነፍ ጥሩ ወቅታዊ አቋም ላይ ሚገኙት መቐለ 70 እንደርታዎች የሊጉ መሪነታቸውን ለማስጠበቅ፣ሰበታዎች ወደ ሊጉ መሪዎች ለመጠጋት ከፍተኛ ፋክክር ያለበት ጨዋታ ያሳያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከጨዋታ ጨዋታ እንደተጋጣሚ አቀራረብ ሚቀያየር አጨዋወትን ሚከተሉት መቐለዎች በነገው ጨዋታ ከሰበታ ተከላካይ ክፍል ጀርባ በሚጣሉ ረጃጅም ቀጥተኛ ኳሶች እድሎችን ለመፍጠር ሊሞክሩ እንደሚችሉ ይገመታል።በተለይ መቐለ ካስቆጠራቸው 12 ግቦች ግማሹን ማስቆጠር የቻለው አማኑኤል ገብረሚካኤል በነገው ጨዋታም ከመስመር እየተነሳ ሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ለቡድኑ የግብ እድል ምንጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት ከባድ አይሆንም።

የኳስ ቁጥጥር ብልጫን ወስደው መጫወትን ምርጫጨው ሚያደርጉት ሰበታዎች በነገው ጨዋት ጥንቃቄ ላይ መሰረት አድርገው መጫወት ግድ ይላቸዋል።በተለይ የመቐለዎችን ፈጣን የማጥቃት ሽግግርን ለማስቆም ከኃላ ሥስት ተከላካዮችን ይጠቀማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምዓም አናብስቶቹ በሜዳቸው 4 ጨዋታዎችን አካሂደው 3 አሸንፈው በአንድ ጨዋታ አቻ ሲለያዩ፤በ4ቱም ጨዋታዎች ላይ 6 ግቦችን አስቆጥረው 2 ግቦች ተቆጥሮባቸዋል።

ሰበታ ከተማ በበኩላቸው ከሜዳቸው ውጪ 3ጨዋታዎችን አካሂደው አንዱ ላይ ሲያሸንፋ ሁለቱ ጨዋታ ላይ ሽንፈት አስተናግደዋል።ከሜዳቸው ውጪ ጥሩ ክብረ ወሰን የሌላቸው ሰበታዎች በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሥስቱ የሜዳቸው ውጪ ጨዋታዎች ላይ ማስቆጠር የቻሉት 1 ግብ ብቻ ነው።

ሚኪኤለ ደስታን በመቐለዎች በኩል ለነገው ጨዋታ ማይደርስ ሲሆን የአጥቂያቸው ኦኪኪ ኦፎላቢ የመሰለፍ ጉዳይም አጠራጣሪ ነው።

የውበቱ አባተ ቡድን ሰበታ አስቻለው ግርማ፣በኃይሉ ቱሳ ና ዳዊት እስጢፋኖስን በጉዳት በነገው ጨዋታ አይጠቀምም።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የ30ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች መናፍ ዐወል (አዳማ ከተማ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ በመድን ሲሸነፍ የጣና ሞገዶች እና ሰጎኖቹ ድል ቀንቷቸዋል

በሊጉ የሳምንቱ የማሳረጊያ ቀናት ሦስት ጨዋታዎች በኢትዮጵያ መድን ፣ ባህርዳር ከተማ እና...