By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ቅድመ ዳሰሳ | ሀዋሳ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
Share
Notification Show More
Latest News
ጋናዊው ተጫዋች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ለመድን ፈረመ
የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች መቐለ 70 እንደርታ ኢትዮጵያ መድህን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
የ23ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
ወልዋሎ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ወልዋሎ ዜናዎች
ሀዋሳ ከተማ ወሳኝ ድል ሲያሳካ አርባምንጭ ሽቅብ መጣሩን ቀጥሏል
አዳማ ከተማ መቐለ 70 እንደርታ የጨዋታ ዘገባ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ አርባምንጭ ከተማ
ንግድ ባንክ ወሳኝ ድል ሲያገኝ ሦስት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል
ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ ኢትዮጵያ መድህን ፋሲል ከነማ ነጌሌ አርሲ ሽረ ምድረገነት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ድሬዳዋ ከተማ ባህርዳር ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግቅዱስ ጊዮርጊስሀዋሳ ከተማቅድመ ዳሰሳ

ቅድመ ዳሰሳ | ሀዋሳ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

Goitom Haile
Goitom Haile 6 years ago
Share
SHARE

ጨዋታ : ሀዋሳ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ
የጨዋታ ቀን: ረቡዕ ታህሳስ 29/2012
የጨዋታ ሰዐት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደ አርቢትር ቢንያም ወርቅአገኘው
ቦታ: ሀዋሳ ኢ/ስታድዮም

ካሳለፍናቸው ሁለት አመታት የሜዳ ላይ ረብሻዎች እና የስፓርታዊ ጨዋነት ችግሮች ስንክሳር የፀዳ የሚመስለው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 7ተኛ ሳምንቱ ላይ ደርሷል።

በዚህ በበዐል ሰሞን መርሀግብር በነገው እለት (ረቡዕ) በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታድዮም በሁለት ጨዋታ ሰባት ግብ ከዘነበባቸው በኋላ በስድስተኛ ሳምንት መርሀ ግብር ወደ መቐለ ተጉዘው ያለ ምንምን ግብ አቻ በውጣት አንድ ነጥብ ይዘው የተመለሱት እና በ8 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማዎች እና ባሳለፍነው ሳምንት የአምናውን ቻምፕዮን መቐለ 70 እንደርታን በሰልሀዲን ሰዒድ እና በአቤል ያለው ግቦች 2-1 በማሸነፍ በሊጉ በ9 ነጥብ 6ተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

በሊጉ ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት የተሳነው ሀዋሳ ከተማ በስድስት ጨዋታዎች ሁለት ጊዜ አሸንፎ ሁለት ጊዜ አቻ ወጥቶ ሁለት ጊዜ ደሞ ሽንፈትን ቀምሷል። በተለይ ደግም በ4ተኛው ሳምንት በኢትዮጵያ ቡና 4 ግብ እና በ5 ተኛው ሳምንት በሲዳማ ቡና 3 ግብ ማስተናገዱን ተከትሎ የቡድኑ የመከላከል ብቃት ጥያቄ ውስጥ ገብቶ ይገኛል። ሆኖም ግን የቡድኑ የማጥቃት ስልት በቂ ግብ እያመረተ አለመገኘቱ የቡድኑ ችግር የመከላከል ስልቱ ላይ ብቻ እንዳልሆን የሚያስያ ነው።

- ማሰታውቂያ -

በአንፃሩ 14ተኛ ዋንጫቸውን ካነሱ በኋላ ከሊጉ ዋንጫ ጋር ለሁለት አመታት የተራራቁት ፈረሰኞቹ በያዝነው የውድድር አመት በ ሰርጂዮቪች መሪነት ዋንጫውን ለማንሳት ተስፋ ያደረጉ ይመስላል ሆኖም በእስካሁኑ የስድስት ሳምንታት ጉዞ ብልጭ ድርግም የሚል ውጤት እያሳዩ ይገኛሉ።

በፈረሰኞቹ በኩል የአስቻለው ታመነ እና የፍሪንፓንግ የተከላካይ ስፍራ ጥምረት እና የሙሉአለም (ዴኮ) ለተከላካዮች የሚሰጠው ሽፋን ግብ ማስቆጠር የተራራ ያህል ከከበደው የዘንድሮው የሀዋሳ ከተማ የማጥቃት ስልት ፈተና ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በሊጉ ልምድ ያላቸውን እና ውጤታማ መሆን የቻሉትን ሁለት አጥቂዎች (ጌታነህ ከበደ እና ሰልሀዲን ሰዒድን) የያዘው የቅዱስ ጊዮርጊስ የአጥቂ ክፍል በተደጋጋሚ መመልከት እንደቻልነው ከአማካኝ ክፍሉ በቂ የሆነ የማግባት እድል እየተፈጠረለት አይደለም አሰልጣኝ ሰርጂዮቪች በነገው እለት ይህንን ችግር ለመቅረፍ ወደ ሜዳ ይዘው ሊገቡት የሚችሉት ስልት ተጠባቂ ቢሆንም መቐለን ከገጠመው ቡድን የተለየ አሰላልፍ እናያለን ተብሎ አይጠበቅም።

ሀዋሳ ከተማዎች ከጨዋታው ሶስት ነጥብ ማግኘት የሚችሉ ከሆነ ወደ መሪነቱ ጎራ መቀላቀል የሚችሉ ሲሆን ቀን ከከዳቸው እና ሽንፈትን የሚቀምሱ ከሆነ ግን የወራጅ ቀጠናውን ሊቀላቀሉ ይችላል። በአንፃሩ ፈረሰኞቹ ድል የሚቀናቸው ከሆነ ወደ ሊጉ አናት የሚጠጉ ሲሆን ሶስት ነጥቡን አሳልፈው የሚሰጡ ከሆነ ደግሞ ከደረጃቸው የሚያሽቆለቁሉበት ሁኔታ የሚፈጠር ይሆናል።

በነገው ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ በኩል የቸርነት አውሽ መግባት አጠራጣሪ ሲሆን በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩልም ረጅም ጊዜ ጉዳት ላይ የነበሩት ግብ ጠባቂው ለዓለም ብርሀኑ እና አማካዩ ናትናኤል ዘለቀ የማይኖሩ ሲሆን የአቡበከር ሳኒም መግባት አጠራጣሪ ነው።

You Might Also Like

ጋናዊው ተጫዋች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ለመድን ፈረመ

የ23ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ወልዋሎ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ

ሀዋሳ ከተማ ወሳኝ ድል ሲያሳካ አርባምንጭ ሽቅብ መጣሩን ቀጥሏል

ንግድ ባንክ ወሳኝ ድል ሲያገኝ ሦስት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
Previous Article ሪፖርት | ስሑል ሽረ ወደ አሸናፊነት መንገድ የተመለሰበትን ድል ሰበታ ላይ አስመዝግቧል
Next Article ቅድመ ዳሰሳ | ባህርዳር ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ለእናንተ ይዛ ነገ ጠዋት ከተፍ ትላለች።

Mussie Girmay By Mussie Girmay 6 years ago
ተወዳጇ ጋዜጣዎ ሀትሪክ ስፖርት ነገ በገበያ ላይ ስትውል የሚከተሉትን ዘገባዎች ይዛሎት ትቀርባለች፤ ከእነዚህ መካከል ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ አባል እና የአርቢትር ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆነው አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ በተለያዩ አነጋጋሪ ጉዳዮች ዙሪያ ከጋዜጣው ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሃቅ በላይ ጋር ቆይታ አድርጎ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽን ሰጥቷል፡፡
የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛሉ
ቅድመ ዳሰሳ | ቅ/ጊዮርጊስ ከ ጅማ አባጅፋር
“ቅ/ጊዮርጊስ ለተጨዋቾቹ ደመወዝ ከመክፈል ባለፈ በተደጋጋሚ ስልክ በመደወል የሚጠይቅበት ሁኔታ የክለቡን ታላቅነት ይበልጥ አሳይቶኛል”ጌታነህ ከበደ /ቅ/ጊዮርጊስ/
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
Welcome Back!

Sign in to your account

Lost your password?