መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ ቅድመ ዳሰሳ | ሀዋሳ ከተማ ከወልቂጤ ከተማ
ሀዋሳ ከተማቅድመ ዳሰሳወልቂጤ ከተማየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቅድመ ዳሰሳ | ሀዋሳ ከተማ ከወልቂጤ ከተማ

አጋራ
አጋራ

 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረጉ ሲሆን ዛሬ (አርብ) አንድ ጨዋታ የተደረገ ሲሆን ነገ (ቅዳሜ) ደግሞ ሰባት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል። በነገው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ሀዋሳ ከተማ ከወልቂጤ ከተማ የሚያደርጉትን ጨዋታ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን እንደሚከተለው ዳሰነዋል። መልካም ንባብ።

ጨዋታ: ሀዋሳ ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ
የጨዋታ ቀን: ቅዳሜ ጥር 09/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ብርሀኑ መኩሪያ
የጨዋታ ቦታ: ሐዋሳ ሰው ሰራሽ ስታዲየም

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ላይ የደረሰ ሲሆን በዚህ ዙርም በስምንተኛው ሳምንት ወደ አዳማ ተጉዘው አንድ ነጥብ ይዘው የተመለሱትና በተከታታይ ጨዋታዎች መከላከል ላይ ያመዘነ ጨዋታ የመረጡ የሚመስሉት የአሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ሀዋሳ ከተማዎች በሜዳቸው ወልቂጤ ከተማን የሚያስተናግዱ ይሆናል።
የፊት መስመሩ በጃኮ አራፋት ላይ መሰረት ያደረጉት ወልቂጤ ከተማዎች ጥሩ የአጨዋወት ዘይቤ ቢኖራቸውም ጎል የማስቆጠር ችግር ይስተዋልባቸዋል። ለዚህም እንደ ማሳያ የሚሆነው ቡድኑ በሊጉ 2ግቦችን ብቻ ማስቆጠሩ ነው። በወልቂጤ ከተማ በኩል እንደ መልካም ዜና የሚነሳው ነገር ቢኖር የተከላካይ ክፍሉ ጥንካሬ ነው። በባለሜዳዎቹ በኩል ግብ የማግባት ብዙም ችግር ያለባቸው አይደሉም። ይህንንም ተከትሎ የነገው ጨዋታ በጉጉት እንዲጠበቅ ያደርገዋል።

በ8ሳምንት የሊጉ ጉዞ ባለሜዳዎቹ ሀዋሳዎች 2ጨዋታዎች አሸንፈው 4ጨዋታዎች አቻ ወጥተው በቀሪዎቹ 2ጨዋታዎች ተሸንፈው መሰብሰብ ከነበረባቸው 24 ነጥቦች 10 ብቻ ሰብስበው 10ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ እንግዳዎቹ ወልቂጤዎች ባንፃሩ ካደረጓቸው 8ጨዋታዎች እንደ ሀዋሳ ሁሉ 2ጨዋታዎችን ማሸነፍ ሲችሉ 2ጨዋታዎች አቻ ተለያይተው በ4ጨዋታዎች ደግሞ ተሸንፈው ከተጋጣሚያቸው ሀዋሳ ከተማ በ2ነጥብ ብቻ ርቀው በ8ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ባለሜዳዎቹ አጥቂያቸው መስፍን ታፈሰን እንዲሁም በተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ጥሩ ብቃት ላይ የነበረውን ግብ ጠባቂውን ቢሊንግ ኢኖህ በነገው ጨዋታ የማያሰልፉ ሲሆን በወልቂጤ በኩል አዳነ በላይነህ እና ቶማስ ስምረቱ በጉዳት የማይሰለፉ ሲሆን አንጋፋው አጥቂ አዳነ ግርማ ሊመለስ እንደሚችል ይጠበቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...