ቅዱስ ጊዮርጊስ ወሳኝ ተጫዋቹን በቶሎ ያገኛል

 

በ 14ኛው ሳምንት የሊጉ መርሀ ግብር ፋሲል ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጎንደር ላይ ባደረጉት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ወቅት በተደጋጋሚ ጊዜ የተጎዳው ጋዲሳ መብራቴ ወዲያውኑ ወደ ጎንደር ሆስፒታል ተወስዶ መታከሙ አይዘነጋም ፡፡

 

አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላም የMRI ምርመራ ተደርጎለት ጉዳቱ አሳሳቢ እንዳልሆነ እና ከሁለት ሳምንታት በኋላ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ታውቋል::

ጋዲሳ መብራቴ በዘንድሮው የውድድር አመት በፈረሰኞቹ ቤት ድንቅ እንቅስቃሴን እያሳየ ሲገኝ ባለፉት የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ለቡድኑ ውጤት የጎላ ሚናን መጫወቱ አይረሴ ነው ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor