By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: “ቅዱስ ጊዮርጊስን ስለመጥቀም እንጂ ኮከብ ጎል አግቢ ስለመሆን አስቤ አላውቅም” አቤል ያለው /ቅዱስ ጊዮርጊስ/
Share
Notification Show More
Latest News
ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ
ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ወልዋሎ
ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ
አዳማ ከተማ መቐለ 70 እንደርታ ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች ድሬዳዋ ከተማ
ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሲዳማ ቡና
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎች

“ቅዱስ ጊዮርጊስን ስለመጥቀም እንጂ ኮከብ ጎል አግቢ ስለመሆን አስቤ አላውቅም” አቤል ያለው /ቅዱስ ጊዮርጊስ/

hatricksport team
hatricksport team 7 years ago
Share
SHARE

በዮሴፍ ከፈለኝ

“
የማን ዩናይትድ ደጋፊ ነኝ ሰራተኛ
በመሆኑና ሰርቶ ለውጤት መብቃትን
ለተጨዋቾች ያሳየ በመሆኑ ከሜሲ ይልቅ
ለሮናልዶ ቅድሚያ እሰጣለሁ” የሚለው
የዋሊያዎቹ የነገ ተስፋ የፈረሰኞቹ ወጣቱ
ኃይል አቤል ያለው ነው፡፡ ከዮሴፍ ከፈለኝ
ጋር በነበረው ቆይታ መሪነቱን መረከባችን
የሚጠበቅ ነው፡፡ ሊጉን አሸንፈን በሻምፒዮንስ
ሊግ የመካፈል ህልማችንን የምናሳካበት
አመት ነው ሲል ለሀትሪክ ተናግሯል፡፡
አቤልና ዮሴፍ ያደረጉት አጠር ያለ ቆይታ
ይህን ይመስላል፡፡

ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ ቡና መሸነፍና
የእናንተ ማሸነፍን ተከትሎ የሊጉ መሪ
ሆናችሁ… ምን ተሰማችሁ?

አቤል፡- የተለየ ስሜት አልተሰማንም….
የጠበቅነው ነገር ነው፡፡ ቀሪ አንድ ጨዋታ አለን
በማሸነፍ ልዩነቱን ለማስፋት እንሞክራለን፡፡
ቡድናችን ገና እየተሰራ ያለ ቡድን እንደመሆኑ
ለወደፊቱ ጠንካራ ሆኖ ከዚህ የተሻለ ብቃት
እንደሚኖረን አልጠራጠርም፡፡

- ማሰታውቂያ -

ሀትሪክ፡- ጊዮርጊስ አንዴ ይምራ እንጂ
እንዴት ዋንጫ ማሸነፍ እንዳለበት ያውቃል
የሚሉ አሉ… ትስማማለህ?

አቤል፡- እውነትኮ ነው ይሄ ባህሪ
ጊዮርጊስን ሳልቀላቀልም አውቀው ነበር
አንዴ ከመራ ጊዮርጊስ አስቸጋሪ እንደሚሆን
ይታወቃል፡፡ ይሄ በዚህ አመትም ይደገማል
ባይ ነኝ፡፡

ሀትሪክ፡- ምርጥ አቋሜ ላይ ነኝ ማለት
ትችላለህ?

አቤል፡- ኧረ አይደለም፡፡ ጠንክሬ
እየሰራሁ በመሆኑ ከዚህ በላይ የተሻለው
አቤል በቀጣዮቹ ጨዋታዎች ይታያል፡
፡ እረፍትና መተኛት እወዳለሁ ይሄ ደግሞ
ለተጨዋች ወሳኝ ነው ልምምዴን ጠንክር
እሰራለሁ የተሻለ ጊዜ ወደፊትም ይኖረኛል፡፡

ሀትሪክ፡- ኮከብ ጎል አግቢ የሆን ህልሙ
አለህ?

አቤል፡- የርሱ ዘመን ወደፊት ይመጣል
ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ አሁን ግን ቅዱስ
ጊዮርጊስን ስለመጥቀም እንጂ ኮከብ ጎል
አግቢ ስለመሆን አስቤ አላውቅም ከዚህ
ይልቅ ሳላሀዲን ሰይድ ልምዱና አቅሙ
ስላለው በኮከብ ጎል አግቢነቱ ይሳካለታል ብዬ
አስባለው፡፡

ሀትሪክ፡- እንደ ቡድን ጫና አለባችሁ?

አቤል፡- ጫና የለብንም እንደ ጊዮርጊስ
ተጫዋችነታችን ግን ሁሉንም ጨዋታ
የማሸነፍ ግዴታ አለብን፡፡

ሀትሪክ፡- በግልስ አቤል ላይ ጫና አለ?

አቤል፡- በፍፁም ጫና የለብኝም…
ደጋፊውም ከጎኔ ሆኖ ስለሚያበረታታኝ ጫና
የለብኝም በቡድኑና በእስካሁኑ ደስተኛ ነኝ
በዚህ አጋጣሚ ደጋፊውን አመሰግናለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- በቡድኑ ውስጥ የተለየ የሆነብህ
ነገር አለ?

አቤል፡- የማሸነፍ ጉጉት…. ፕሪሚየር
ሊጉን አሸንፈን ወደ አፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ
የማለፍ ጉጉት አለብን፡፡

ሀትሪክ፡- የዋንጫ አሸናፊ ነን ለዚህ
ጥርጥር የለም የሚሉ ድምጾች እየተሰሙ
ነው… እናንተ ጋር ይሄ ስሜት አለ?

አቤል፡- ጨዋታው ገና ነው ነገር ግን
ቡድናችን የዋንጫ ቲም ነው ከፊታችን
ያሉትን ጨዋታዎች እያሸነፍን ሄደን
ዋንጫውን እንደምንወስድ እምነቱ አለን፡፡

ሀትሪክ፡- በክልል ማሸነፋችሁ
ጥንካሬያችሁን አያሳይም?

አቤል፡- ይሄማ ምን ጥርጥር አለው…
ጠንካራ ሊግ እንደመሆኑ ፉክክሩ ጨምሯል
በክልል ማሸነፍ ከባድ ቢሆንም ክልል ላይ
እያሸነፍን መሆኑ የዋንጫ ቡድን መሆናችንን
ያሳያል፡፡

ሀትሪክ፡- ለደጋፊያዎቻችሁ የምትለው
ነገር አለ?

አቤል፡- በክልልም ሆነ በአዲስ አበባ
ጨዋታ ባለብን ቦታ ሁሉ እየተገኙ
ደግፈውናል ዋንጫ ይገባቸዋል ለድጋፋቸውም
ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ በቀጣይ ጨዋታዎች
ከፈጣሪ ጋር የሚያቆመን አይኖርም ብዬ
አምናለው የሁልጊዜ ድጋፋቸው አይለየን
ማለት እፈልጋለው።

You Might Also Like

ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ

ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ

ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ

ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ

ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By hatricksport team
Follow:
Hatricksport team
Previous Article የ2011 ኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 14ኛሳምንት ጨዋታዎች በቀጥታ /LIVESCORE/ ይከታተሉ
Next Article ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ማክሰኞ ገበያ ላይ በሳምንት አንድ ቀን ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ እና ባለቀለሟ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማክሰኞም ገበያ ላይ ስትውል ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን?

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስ

ቅዱስ ጊዮርጊስ የዳኝነት በደል ደርሶብኛል በማለት ቅሬታውን አቀረበ

Habtamu Mitku By Habtamu Mitku 1 year ago
መድን ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል
“ማሸነፍ የነበረብንን ጨዋታ በዳኛዋ ተነጥቀናል፤ ፍፁም ቅጣት ምቱ አያሰጥም” ሄኖክ አዱኛ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
“መልክህ አላማረኝም ብለው የተነሱ ደጋፊዎች ቢኖሩም ሁሉንም
በውጤት ለማሳመን ጠንክሬ እየሰራሁ ነው”አሰልጣኝ ስዩም ከበደ (ፋሲል ከነማ)
ሳለሀዲን ሰኢድ ከፈረሰኞቹ ጋር ሁለት አመታት ለመቆየት ተስማማ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
Welcome Back!

Sign in to your account

Lost your password?