መነሻ ገጽ ዜናዎች  ሽሬ እንዳስላሴ የእግር ኳስ ቡድን አንድ ዘመናዊ አውቶቡስ በእርዳታ አገኘ
ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

 ሽሬ እንዳስላሴ የእግር ኳስ ቡድን አንድ ዘመናዊ አውቶቡስ በእርዳታ አገኘ

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በመሳተፍ ላይ የሚገኘው ስሑል ሽሬ የእግር ኳስ ቡድን ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው ዘመናዊ አውቶቡስ በእርዳታ አገኘ።

ዘመናዊ አውቶቡሱን ለቡድኑ ያበረከተው በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የሚገኝ የዳሽን ቢራ ማከፋፈያ አክሲዮን ማህበር ነው።

በስጦታ የተገኘው ዘመናዊ አውቶብስ የእግር ኳስ ቡድኑ ቀደም ሲል የነበረበትን የትራንስፖርት ችግር እንደሚፈታለት የክለቡ ምክትል አስልጣኝ በረከት ገብረመድህን ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ አውቶብሱ የተጫዋቾችን ሞራል ለመገንባትና ከቦታ ወደ ቦታ በምቾት ለመጓጓዝ ጠቀሜታ እንዳለው ነው የገለጹት።

ለተለያዩ ድርጅቶች በተደጋጋሚ ያቀረቡትን የተሽከርካሪ ድጋፍ ጥያቄ ማህበሩ በአግባቡ ሰምቶ ዘመናዊ አውቶቡስ በማበርከቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው የገለጸው ደግሞ የቡድኑ አምበል ወጣት መብራህቶም ፍስሃ ነው።

ዘመናዊ አውቶቡሱ ባለ 49 መቀመጫ ወንበር፣ ፍሪጅ፣ የሻይ ማሞቂያ ማሽንና ቴሌቪዥን የተገጠመለት ነው።

የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ መኮነን ገብረሕይወት በበኩላቸው የእግር ኳስ ቡድኑ ያለበትን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ ሲባል ዘመናዊ አውቶቡሱን ገዝተው ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም አውቶቡሱ የእግር ኳስ ቡድኑ ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪሚየርሊግ እንዲያድግ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድጋፍ ለማበርከት በሚል እሳቤ መሆኑንም ተናግረዋል።

እንደአቶ መኮንን ገለጻ ቀደም ሲልም ማህበሩ ከ200 ሺህ ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ ለእግር ኳስ ብድኑ ድጋፍ አድርጓል።

ስሑል ሽሬ የእግር ኳስ ብድን ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች እየቀረው ከምድቡ በስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

Source-ENA

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ አስፈረመ

መሳይ አያኖ አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና የግብ ዘብ ሆኗል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፈው...

ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

በዮሴፍ ከፈለኝ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ...

ዜናዎችየዲሲፕሊን ውሳኔዎች

27ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አብዱላጢፍ ባምባ (መቐለ 70 እንደርታ) : ክለቡ ከ ወልዋሎ አዲግራት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...