የክረምት ዝውውርን ዘግይተው የተቀላቀሉት ሽሬ እንዳስላሴ ሄኖክ ካሳሁንን ስድስተኛ ፈራሚያቸው ማድረግ ችለዋል።የመጀመርያ ኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ተሳትፎዋቸውን እሚያደርጉት ሽረ እንዳስላሴ ከቀድሞው የደደቢትና ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ተጨዋች ሄኖክ ካሳሁን ውጪ አምስት ተጨዋቾችን ማስፈረማቸውን እሚታወስ ነው።
የደደቢት ኣካዳሚ ውጤት የሆነው ሄኖክ ደደቢት እያለ አብሮት ከሰራው ከቀድሞ አሰልጣኙ ዳንኤል ፀሃየ ጋር ዳግም እሚገናኝ ይሆናል።