ሶስት የአዳማ ከተማ ተጫዋቾች ለክለቡ የመልቀቂያ ወረቀት አስገብተዋል

 

የፊት መስመር አጥቂው ዳዋ ሆቴሳ አማካዩ ከንአን ማርክነህ እና ተከላካዩ ምኞት ደበበ በደሞዝ ችግር ምክንያት ክለቡ እንዲያሰናብታቸው የመልቀቂያ ወረቀት አስገብተዋል።

አዳማ ከተማ ወሳኝ ተጫዋቾቹን ሊያጣ የተቃረበ ይመስላል። የሶስት ወር ደሞዝ ያልተከፈላቸው ሶስቱም ተጫዋቾች የመልቀቂያ ደብዳቤ ለማስገባት እንደምክንያትነት የተገለፀ ሲሆን። ከዚህ ቀደም ክለቡ ከፍተኛ ደሞዝ ተጫዋቾችን እየከፈለ ለማቆየት የፋይናንስ ችግሩ እንደሚያዳግተው ክለቡ የገለፀ መሆኑ ይታወሳል። በዚህም ምክንያት ከተጫዋቾቹ ጋር የመለያየቱ ነገር እርግጥ ያደርገዋል። የክለቡ አመራሮች ባስገቡት የመልቀቂያ ደብዳቤ ተነጋግረው ምላሽ እንደሚሰጣቸው ተነግሯቸዋል። የመጨረሻውን ውሳኔ ተከታትለን ወደ እናንተ የምናደር መሆናችንን ከወዲሁ ለመግለፅ እንወዳለን።

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport