ስሑል ሽረ ግዙፉን ተከላካይ አስፈርሟል

 

ስሑል ሽረዎች ደስታ ጊቻሞን የቡድኑ አራተኛ ፈራሚ አድርገዋል።

ለየኢትዮጵያ መድን፣ሻሸመኔ ከተማ፣አዳማ ከተማ ፣ደቡብ ፖሊስ፣ሀድያ ሆሳዕናና እና የወጣት እና ወናው ብሄራዊ ቡድን መጫወት የቻለው ይህ የመሀል ተከላካይ አምና ደቡብ ፖሊስ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱን ተከትሎ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ሀድያ አምሮቶ በመጀመሪያው ዙር ድንቅ ብቃትን በማድረግ ከመከላከሉ በዘለለ ወደ ፊት በመሄድ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

በዚህ ሳምንት ከክለቡ ጋር በስምምነት የተለያየው ደስታ ጊቻሞ አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀምን በዋና አሰልጣኝነት ከቀጠሩ በኋላ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ጠንካራራ ተፎካካሪ ሆነው ለመቅረብ ያሰቡት ሽሬዎች የተከላካይ መስለመራቸውን በደምብ ሊያጠናክርላቸው የሚችል ተጫዋች ይሆናል።

ስሑላውያኑ  ራሂም ኦስማን፣ዮናታን ከበደ እና አስራት መገርሳን አስፈርመው እንደነበር ይታወሳል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor