ስሑል ሽረ ጋናዊ አጥቂ አስፈርሟል !

በአሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀ የሁለተኛው ዙር የውድድር አጋማሽ የሚመሩት ሽረዎች ጋናዊን ራሂም ኦስማኑን ማስፍረማቸው ታውቋል ::

ከሳሊፍ ፎፎና ጋር በዝውውር መስኮቱ የተለያዩት ሽረዎች የፊት መስመራቸውን ማጠናከራቸውን ሲቀጥሉ ከዮናታን ከበደ በመቀጠል ራሂም ኦስማኑን ማስፈረም ችለዋል ::

ራሂም ኦስማኑን ከዚህ ቀደም ለዛምቢያው ሀያል ክለብ ዜስኮ ዩናይትድ መጫወት ሲችል በፈረንጆቹ የዝውውር መስኮት የአልጄሪያውን ክለብ በ 10,000 ዶላር ለመቀላቀል ቢስማማም የወረቀት ጉዳዮች ሳይጠናቀቁለት የዝውውር መስኮቱ መዘጋቱን ተከትሎ ስሑል ሽረን ሊቀላቀል ችሏል ::

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team