በአሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀ የሚመሩት ስሑል ሽረወዎች ከመስመር ተጫዋቻቸው ጋር መለያየታቸው ተሰምቷል ።
በሊጉ ልምድ አላቸው ከሚባሉ የውጭ ሀገር ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ያስር ሙገርዋ ከክለቡ ጋር መለያየቱን ይፋ አድርጓል ።
ያለፉትን ዓመታት በስሑል ሽረ ጥሩ ዓመትን ያሳለፈው ያስር ሙገርዋ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ከክለቡ ጋር መለያየቱን ሲያሳውቅ የክለቡን አመራሮች ፣ ደጋፊዎች ፣ ሰራተኞች አመስግኗል ።
ያስር ሙገርዋ በፕርሚየር ሊጉ ለቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ መጫወት ሲችል ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣየቱ አስቀድሞ በደቡብ አፍሪካ ለኦርላንዶ ፓይሬትስ መጫወቱ ይታወሳል ።
አስተያየት ይስጡ