ሴቶች አንደኛ ዲቪዚዮን | ሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድባንክ በሜዳቸው ሲያሸንፉ መቐለ 70 እንደርታ ከሜዳው ውጭ በማሸነፍ ወደ ድል ተመልሰዋል

 

በ 11ኛ ሳምንት የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ አደማ ከተማን አስተናግዶ 2-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

 

የመጀመሪያዎቹ 25 ደቂቃዎች ምንም እንኳን ሁለቱም ቡድኖች ግብ ማግባት ቢችሉም በእንቅስቃሴ ደረጃ ግን እጅጉኑ ሳቢ ያልነበረ ነው ማለት ይቻላል። 14ኛው ደቂቃ ላይ ቅድስት ዘለቀ ሳጥን ውስጥ መሬት ለመሬት አክርራ መትታ ኳስ እና መረብን በማገናኘት ሀዋሳን ቀዳሚ አድርጋለች። ከአስራ አንድ ደቂቃዎች በኋላ ምርቃት ፈለቀ በግምት 26 ሜት ርቀት ላይ የተገኘውን የቅጣት ምት በቀጥታ ወደ ግብ መትታ አባይነሽ ኤርቄሎ ለማዳን ያደረገችው ጥረት ሳይሳካላት ቀርቶ ኳስ እና መረብን በማገናኘት ቡድኗን አቻ ማድረግ ችላለች።

ቀስ በቀስ ወደ ወደ ጨዋታ ቅኝት የገቡት ባለሜዳዎች ኳስን ተቆጣጥረው በመጫወት ማራኪ ቅብብልን በማድረግ ቶሎ ወደ ግብ ቢደርሱም ተመልካቹን ከማዝናናት ውጭ ውጤታማ አልነበሩም። በአንፃሩ አዳማ ከተማዎች በረጃጅም ኳሶች ወደ ተቃራኒ የግብ ክልል ለመድረስ ጥረት አድርገዋል። ሀዋሳ ከተማች አስቆጪ ሙከራ ሳይጠቀሙበት ቀርተው በጋራ የ 1-1 ውጤት ለእረፍት ወጥተዋል።

እንደ መጀመሪያው አጋማሽ ሁሉ በዚህኛው አጋማሽ የተቀዛቀዘ ጅማሮ ቢኖረውም በሁለተም በኩል ጥሩ የኳስ ቅብብሎሽ ቢደረጉም ፍሪያቸው ግን እዚህ ግባ የሚባሉ አልነበሩም። በተለይ በማራኪ ቅብብል ሀዋሳ ከተማዎች የሚያገኟቸውን ኳሶች ወደ ቀኝ መስመር አጋድለው በቀጥታ ወደ ሳጥኑ ሲጥሏቸው የነበሩ ኳሶች በቀላሉ ለአዳማ ከተማ ተከላካዮች ሲሳይ ሲሆኑ ተስተውለዋል። በዚህ አጋማሽ ብቸኛ ኢላማዋን የጠበቀች ሙከራ ማድረግ የቻሉት ባለሜዳዎቹ በድጋሚ መሪ የሆኑበትን ግብ አግንተዋል። 79ኛው ደቂቃ ዙፋን ደፈርሻ ከነፃነት መና የቀበለቻትን ጥሩ ኳስ ሶስት ግዜ ገፋ በማድረግ ከሳጥን ውጭ አክርራ መትታ ግብ በማስቆጠር ሀዋሳን መሪ አድርጋለች።

በሀዋሳ በኩል ነፃነት መና ነፃ የማግባት አጋጣሚ ሳትጠቀምበት ስትቀር። ከቀኝ መስመር እፀገነት ብዙነህ ያሻገረችላትን ኳስ ተጠቅማ በግንባሯ ገጭታ ወደ ውጭ የወጣችባት በአዳማ በኩል አቻ ልታደርጋቸው የምትችል አጋጣሚ ነበረች። ጨዋታው ተጨማሪ ግቦች ሳይስተናገዱበት በሀዋሳ ከተማ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

 

ሌሎች የ 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም ሲደረጉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በረሂማ ዘርጋው እና ገነሜ ወርቁ ሁለት ግቦች ተከታያቸው ጌዲኦ ዲላን 2-0 በማሸነፍ መሪነታቸውን ሲያጠናክሩ። ከተታታይ ነጥብ መጣሎች በኋላ መቐለ 70 እንደርታዎች አዲስ አበባ ከተማን 2-0 በማሸነፍ ወደ ድል ተመልሰዋል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor