ጳጉሜ 4 በሃዋሳ ኢንተርናሽናል ስታድየም ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የምትገጥመው ሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድንዋ ለጨዋታው ለመዘጋጀት ለ35 የውጭ ሃገር ተጨዋቾችዋ ጥሪ ኣደርጋለች።በኢንግሊዝ ቻምፒዮንስ ሺፕ ሚጫወቱት የኮቨንትሪ ሲቲው ኣጥቂ ኣሟዱ ባካዮኮ፣የኩዊን ፓርክሬንጀርስ ተከላካይ ኦስማን ካካይ እና የብሪስቶል ሲቲ ግብ ጠባቂ ኣልሃጂ ሴሳይ ለብሄራዊ ቡድኑ ለመጀመርያ ጊዜ ጥሪ ተደርጎላቸዋል።በተጨማሪም በዴንማርክ ሊግ ለኤጂኤፍ ኣርሁስ ሚጫወተው ሙስጠፋ ቡንዱ፣በኤምኤልኤስ(MLS) ለቶሮንቶ ሚጫወተው ኬይ ካማራ፣የኤፍሲ ዙሪክ ተከላካይ ኡማሩ ባንጉራ ለብሄራዊ ቡድኑ ጥሪ ከተደረገላቸው ተጨዋቾች ሚጠቀሱት ናቸው።

የምድብዋ የመጀመርያ ጨዋታ ኬንያን በማሸነፍ የጀመረችው ሴራሊዮን ጻጉሜ 4 በጆን ኬይስተር እየተመራች አብርሃም መብራህቱን ኣዲስ አሰልጣኝ ኣድርጋ የሾመችውን ኢትዮጵያን ይገጥማሉ።
አስተያየት ይስጡ