ሳምንታዊ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ነገም ማክሰኞ ታህሳስ 3/2010 ዓ.ም በማለዳው በእጅዎ ልትገባ መሰናዶዋን አጠናቅቃለች፡፡
ለመሆኑ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?
-ከሀገር ውስጥ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 6ኛ ሳምንት እሁድ ሊካሄድ የነበረው የሸገር ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነገ 11:00 ሰዓት የሚያደረጉት ጨዋታ ከወዲሁ አጓጊ ሆኖል፡፡ የሁለቱ ክለብ ተጨዋቾች ስለ ደርቢው ጨዋታ ምን አሉ ነገ ማለዳ ይጠብቁን!
ከባህር ማዶ፡- በሳምንቱ መጨረሻ በኦልድ ትራፎርድ ማንቸስተር ዮናይትድ በማንቸስተር ሲቲ የደረሰባቸውን አሳዛኝ ሽንፈት አስመለክቶ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ዳኛውን ወቅሰዋል። ኒኮላስ ኦታሜንዲ በጨዋታው ደምቆ አምሽቷል። ዳሰነዋል።
የግል ክብሮች እየጎረፉለት ያሉት ክርስቲያኖ ሮናልዶ እንዲሁም ተቀይሮ በመግባት አርሰናልን ከሽንፈት እየታደገ የሚገኘው ኦሊቬ ዥሩ ሰፋ ባለ ዘገባዎች ተዳስሰዋል።
እናም ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን ነገ ማለዳ ይዛ እጅዎ ትገባለች፡፡
በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት www.hatricksport.com ድህረ-ገፃችን ይጎብኙን፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ

አስተያየት ይስጡ