ሳምንታዊ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ነገም ማክሰኞ ጥር 08/2010 ዓ.ም በማለዳው በእጅዎ ልትገባ መሰናዶዋን አጠናቅቃለች፡፡
ለመሆኑ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?
-ከሀገር ውስጥ፡- አሁንም ውዝግብ ያላጣው እና ለሶስተኛ ጊዜ ስለተራዘመው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝደንት እና ስራ አስፈፃሚ ምርጫ ጋር በተያያዘ የሸዋረጋ ደስታ አነጋጋሪ ቃለ ምልልስ በተለይ ከሀትሪክ ስፖርት ጋር። “ሶስት ሺህ ብር ለማግኘት አፋር ሳይሄዱ ሄደናል ብለው የዋሹ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ድምፃቸውን በገንዘብ አይሸጡም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው።” ብሏል።
ከባህር ማዶ፡- የማንቸስተር ሲቲን ያለመሸነፍ ጉዞ የገታው ሊቨርፑል አሸናፊነት ሚስጥር፤ “ያለ ኩቲንሆ ማሸነፍ እንደምንችል አሳይተናል፡፡” የርገን ክሎፕ
የአርሰናሉ ጃክ ዊልሼር ዳግም ውልደት፣ የአንቶኒዮ ኮንቴ አስተያየት እና ሌሎችም ዜናዎች
በኦልዲስ በት ጉዲስ አምዳችን ደግሞ “አልጄሪያዎች እናንተ ሩጫ እንጂ ኳስ አትችሉም ብለውን ያሸነፍናቸው ጊዜ መቼም አልረሳውም።” ከሚለው የቀድሞ ተጫዋች ብዙነህ ወርቁ (በሶ) ጋር ቆይታ አድርገናል።
እናም ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን ነገ ማለዳ ይዛ እጅዎ ትገባለች፡፡
በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ይጎብኙን፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ

አስተያየት ይስጡ