መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ሳምንታዊዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሳምንታዊዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ

አጋራ
አጋራ

ሳምንታዊዋ እንደዚሁም ተወዳጇ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ነገም ማክሰኞ ጥር 22/2010 ዓ.ም በማለዳው ከእጅዎ ልትገባ መሰናዶዋን አጠናቅቃለች፡፡
ለመሆኑ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?
-ከሀገር ውስጥ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ተሳትፎአቸውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ቡናው የአማካይ ስፍራ ተደናቂ ተጨዋች የሆነው መስዑድ መሐመድ ስለ ክለባቸው አቋምና በውድድሩ ላይ ስለሚያመጡት ውጤት አስመልክቶ አስተያየቱን የሰጠ ሲሆን ከእነዚያ ውስጥም ‘‘አትጠራጠሩ ምርጥ ስብስብና ጎበዝ አሰልጣኝ ስላለን የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ እናነሳለን።” ያለበት ዘገባ ቀርቧል፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ሌላው የነገ ዘገባ ውስጥ በዘንድሮ የሊጉ ውድድር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በወላይታ ድቻ ሽንፈት ስላስተናገደው የቅ/ጊዮርጊስ ክለብም የቡድኑ ስኬታማ የኮሪደር ስፍራ ተጨዋች ከሆነው በኃይሉ አሰፋ /ቱሳ/ ጋርም ስለጨዋታውና በሌሎች ተያያዥ በሆኑ ጥያቄዎች ዙሪያም ቆይታ አድርገን ተጨዋቹ ምላሹን ሰጥቷል፤ ሀትሪክ ከእዚያ ውጪም ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችንም ልታስነብቦት ከጫፍ ደርሳ ወደ ማተሚያ ቤት ገብታለች፡፡

ከባህር ማዶ፡- የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን አስመልክቶ በሰሞኑ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ከአርሰናል ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ የተዘዋወረው አሌክሲስ ሳንቼዝ ‘‘ማንቸስተር ዩናይትድን የመረጥኩት ዋንጫዎችን ለማንሳት ስለምፈልግ ነው” የሚል ሰፋ ያለ መግለጫን የሰጠ ሲሆን በተቃራኒው ከማንቸስተር ዩናይትድ ወደ አርሰናል የተዘዋወረው ሄንሪክ ሚኪታሪያን ‘‘በአርሰናል መለያ የመጀመሪያ ጨዋታዬን ለማድረግ ጓጉቻለሁ።” ያለበትን ጣፋጭ ዘገባም ይዘንላችሁ ቀርበናል፤ ከእዚያም ባሻገር የቼልሲው ተከላካይ ዴቪድ ዛፓኮስታም አንቶኒዬ ኮንቴ ሙሉ አሰልጣኝ ነው በማለት ስለ እሱና ስለቡድናቸው አስተያየትን የሰጠበትም ዘገባ የቀረበ ሲሆን፤ ከእዚያ ውጪም ሌሎች ያልተሰሙ አስተያየቶችና ዜናዎችም በጋዜጣው ሊቀርብላችሁ በቅቷል፡፡

በኦልዲስ በት ጉዲስ አምዳችንም የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና በክለብ ደረጃም ለተለያዩ ቡድኖች በመጫወት ያሳለፈው ጌታሁን መንግስቱ በስኬትም በውድቀትም ስለታጀበው ጣፋጭ፣ አዝናኝ፣ አሳዛኝ እና መሳጭ ስለሆነው አስገራሚው የእግር ኳስ ሕይወቱ ከሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ከሆነው ጋዜጠኛ ይስሃቅ በላይ ጋር ቆይታ አድርጎ ምላሹን ሊሰጥ ችሏል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጨዋች ጌታሁን መንግስቱ በተጨዋችነት ዘመኑ ብዙዎች ያደንቁት የነበረ ሲሆን ኳሱን ካቆመ በኋላ ወደ ጎዳና ጭምር በመውጣት አስከፊ የሆነ ህይወትን ሊያሳልፍ ችሏል፤ ይህ ተደናቂ የቀድሞ ተጨዋች ከተናገረው ውስጥም “ለሰባት ወራት ፈታኝና መራራ የጎዳና ሕይወት መርቻለሁ፤ ሰባት ጊዜም ወድቄያለው፤ በስምንተኛው ግን እነሳለሁ።” ይላል።

ሀትሪክ ነገ በፍፁም አታምልጦት፤ ሌሎችም ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችንም ይዛ በማለዳው እጅዎ ትገባለች፡፡
በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.com ድረ-ገፃችን መከታተል ትችላላችሁ፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገ ማክሰኞ ጥር 22/2010 ዓ.ም የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...