መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ሳምንታዊዋና ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገ ማክሰኞ የካቲት 13/2010 እትሟ
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ

ሳምንታዊዋና ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገ ማክሰኞ የካቲት 13/2010 እትሟ

አጋራ
አጋራ

ሳምንታዊዋና ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገ ማክሰኞ የካቲት 13/2010 እትሟ እንደተለመደው ሁሉ የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ስፖርት ዘገባዎችን በአማረና በልዩ መልኩ ልናስነብባችሁ ተቃርበን ስራችን ወደ ማተሚያ ቤት አምርቷል፤ ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትም የሀገር ውስጥ ዘገባዋ ከምታስነብባችሁ ጉዳዮች መካከል የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አብነት ገ/መስቀል ክለቡ ከአዳማ ከተማ ጋር ተጫውቶ ግጥሚያውን 1-1 ካጠናቀቀ በኋላ የአዲስ አበባ ስታዲየም ላይ በተነሳው የደጋፊዎች ብጥብጥና ጉዳት እንደዚሁም ደግሞ በክለባቸው ወቅታዊ አቋም ዙሪያ ለሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ልዩ ቃለ-ምልልስ በማድረግ ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል፤ አቶ አብነት ከሰጡት ቃለ-ምልልስ ውስጥም ‘‘ከአዳማ ጋር በነበረው ጨዋታ በደጋፊዎች ላይ በደረሰው ጉዳት ከልብ አዝኛለሁ”፤ ‘‘በጨዋታው የደጋፊዎች ቁጣ የገነፈለበት ምክንያት ይገባናል፤ ግን ደጋፊው ስሜቱን መግለፅ ያለበት በጨዋነትና በክለቡ ባህል መሰረት ነው”፤ የሚሉና  ‘‘ቅ/ጊዮርጊስ እንዴት ከችግር ወጥቶ ውጤታማ መሆን እንደሚችል ጠንቅቆ የሚያውቅ ክለብ በመሆኑ ብዙም አንሰጋም” በማለት የሰጡት ምላሽም ይገኛል፤ የነገ እትም ሀትሪክን አንብቧት፤ ከዚህ በተጫማሪ ሀትሪክ በነገው እትሟ ኢንስትራክተር ፍቃዱ ግርማም የአገራችንን ዳኝነት አስመልክቶም ‘‘የእኛ ሀገር ዳኞች የስነ-ልቦና ችግር ያለባቸው ናቸው” በማለት የሰጡትም ቃለ-ምልልስ የሚገኝ ሲሆን ከእዚያ ባሻገር ደግሞ የቀድሞ እግር ኳስ ተጨዋቾችን በምናስታውስበት የኦልዲስ በት ጉዲስ አምዳችን ላይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተደናቂ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች የሆነው ታምሩ ያደታም የኳስ ሕይወቱን የሚዳስስ ቃለ-ምልልስን ከጋዜጣችን ጋር አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጨዋች ታምሩ በእግር ኳስ ሕይወቱ ለስምንት ለሚደርሱ ክለቦች ኳስን በጥሩ ብቃቱ የተጫወተ ሲሆን ያ እንደሚያስደስተውና ሆኖም ግን ከተጫወተባቸው ክለቦች መካከል አራቱ በመፍረሳቸውና የአሁን ሰዓት ላይ በሀገሪቱ ውስጥ ቡድኖቹ አለመኖራቸው እንደሚያሳዝነውና እንደሚያስቆጨውም ይናገራል፡፡

ሀትሪክ ስፖርት ከባህር ማዶ ዘገባዎቿ መካከል ደግሞ  የሊቨርፑሉ መሐመድ ሳላህ  የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ጉዞን በማስመልከት ዘገባን ይዘንላችሁ የቀረብን ሲሆን ከእዚያ ውጪም በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬና ነገ ምሽት ከሚከናወኑት ግጥሚያዎች መካከል ባርሴሎናና ቼልሲ፤ ሲቪያና ማንቸስተር ዩናይትድ ስለሚያደርጉት ጨዋታም የሚወዱት ዘገባ ቀርቦላችኋል፤ የነገው ሀትሪክ እንዳታመልጦት ፡፡

በአውሮፓ የተለያዩ ሀገራት ስለተካሄዱ የውስጥ ውድድሮችም መረጃዎችን ይዛሎት ቀርባለች፤ ሀትሪክ የእናንተ ናት ይወዷታል፤ ያንብቧት ሀትሪክ ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን ይዛሎት ቀርባለች፡፡

በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ይጎብኙን፡፡

ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡

መልካም ንባብ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...