ሳሊፍ ፎፋና ወደ ሀድያ ሆሳዕና አምርቷል

 

ሀድያ ሆሳዕና አይቮሪኮስታዊውን አጥቂ ሳሊፍ ፎፋና ወደ ቡድናቸው ቀላቅሏል።

ከሲዳማ ቡና ከተለያየ በኋላ ወደ ስሑል ሽረ በማምራት በሁለተኛው ዙር አስራ አንድ ግቦችን በማስቆጠር ስሁል ሸረን ከመውረድ የታደገው ይህ ጨዋታ በሊጉ ግርጌ ለሚገኘው ሀድያ ሆሳዕና ደካማው እና ግብ የማስቆጠር ከፍተኛ ክፍተት ችግር ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል።

በመጀመሪያው ዙር 11 ግቦችን ብቻ ያስቆጠረው ክለቡ ከሳሊፍ ፎፋና መምጣት በኋላስ ምን ይሆን የሚለው ተጠባቂ ያደርገዋል።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor